You are here

በጎንደር ከተማ የጠራውን ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ

የሰማያዊ ፓርቲ መንግስት ከህዝብ ጀርባ የሚያካሂደውን የኢትዮጵያ - ሱዳን ድንበር ማካለልን በመቃወም በጎንደር ከተማ የጠራውን ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል በእለቱም የፓርቲው አስተባባሪ ለህብረተሰቡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅትና አምባገንን ስርዓት ውስጥ ሆናችሁ የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል ብላችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን በሚል ንግግር ፕሮግራሙን ከፍተው የሰልፉን አላማ አብራርተው የፓርቲውን ሊቀመንበር ወደ መድረክ ጋብዘዋል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበርም ለተሰላፊዎቹ ባስተላላፉት መልእክት ለወጣቶች የሀገራቸውን ክብር እንዲያስጠብቁ እራሳቸውንም ከፍርሀት እና ከስጋት በማላቀቅ ለራሳቸውም ለሀገራቸውም አለኝታ እንዲሆኑ፤ እንዲሁም ስርዓቱ ላይ ያሉት አስተዳደሮች ስልጣን ወቅታዊ መሆኑን አውቀው በኢትዮጵያ ድንበር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ደባ እንዲያስቆሙ ከታሪክ ተጠያቂነት እንዲድኑ፤ ለልጆቻቸውም ውርደትን ሳይሆን ክብርን እንዲያወርሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ፓርቲውም የጠራውን ሰልፍ እና ማስተላለፍ የፈለገውን መልእክት በተሳካ ሁኔታ አስተላልፎ ፕሮግራሙን አጠናቋል፡፡ ፓርቲውም በአካባቢው የሚገኙ የፓርቲው አስተባባሪዎችን እንዲሁ የጎንደር እና የአካባቢው ህዝብን ለዚህ ሰልፍ መሳካት ላደረጉት አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርቧል፡፡