You are here

የሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ቅስቀሳ መግለጫ

ምንም እንኳ ሰማያዊ ፓርቲ ሲቋቋም በኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት በሚያደርገው ትግል በሁሉም ዘርፎች ግልፅ እና ዝርዝር የሆኑ አማራጭ የፖሊሲ ሃሳቦችን ያዘጋጀ ቢሆንም በያዝነው ዓመት ለሚካሄደው ምርጫ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምርጫ ቅስቀሳ መግለጫ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ እንደሚታወቀው አሁን ሀገሪቱ የምትመራበት ሕገመንግስት በየአምስት ዓመቱ በሚካሄድ አጠቃላይ ምርጫ መንግስት እንዲመሠረት የሚፈቅድ በመሆኑ እና ይህም በትክክል ተግባራዊ ከሆነ ሀገሪቱን በየአምስት ዓመቱ አፍርሶ የመሥራት የሚመስል ውጤት እንዳያስከትል ጥንቃቄ መወሰድ እንዳለበት ስለታመነበት ሲሆን መራጩ ሕዝብም ከዚህ መግለጫ ተገቢ ግንዛቤ አግኝቶ የሀገሩን መፃዒ ዕድል በተመለከተ የተሻለ ርዕይና አመለካከት ላለው ሰማያዊ ፓርቲ ድምፁን እንዲሰጥ ለማስቻል ነው፡፡
መግለጫው በአራት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ተዘጋጅቷል፡፡ የመጀመሪያው የሀገሪቱን ፀጥታ ደህንነት እና ዳር ድንበር በተመለከተ፤ ሁለተኛው የሀገሪቱን ሕግጋት የፍትሕ ሥርዓት የዜጎች ዴሞክራሲና ነፃነትን በተመለከተ፤ ሦስተኛው የሀገሪቱን የመንግስት አስተዳደርና አመራር በተመለከተ እንዲሁም አራተኛው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ሚና እና የአባላቶቻቸውን ተሳትፎ በተመለከተ ሲሆኑ ዝርዘሩ በተራ ቁጥር 6 ስር ተብራርቷል፡፡
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ