You are here

የሰማያዊ ፓርቲ የጋሞጎፋ ዞን አመራሮች ታሰሩ

አርባ ምንጭ ከተማ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ የዞኑ አስተባባሪዎች በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸው ታወቀ፡፡ ትናንት ሐምሌ 29 ሌሊት የዞኑ ሊቀመንበር አቶ ሉሉ፣ አቶ ፈቃዱ አበበና አቶ ጌታሁን በየነ ከየ ቤታቸው በፖሊስ ተይዘው ወዳልታወቀ ቦታ የተወሰዱ ሲሆን አሁን ያሉበት ቦታ እንደማይታወቅ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
አመራሮቹ በፖሊስ በተያዙበት ወቅት ቤታቸው እንደተበረበረና የፓርቲው አባላት አርባ ምንጭ በሚገኘው የፓርቲው ቢሮ እንዳይገቡ ቢሮውን ከበው የሚገኙ ፖሊሶች እየከለከሉ መሆኑም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሌላ በኩል በዞኑ በየ ወረዳው የሚገኙትን የፓርቲው አባላት ከሰማያዊ ፓርቲ እንዲወጡ ጫና እየጠደረገባቸው እንደሚገኝ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ገልጸዋል፡፡