የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አባላት ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

የቀድሞው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አመራርና አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላለቀላቸውን የሰማዊ ፓርቲ አመራሮች በትላንትናው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

በመኢአድ ፅህፈት ቤት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራሪያ የሰጡት የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ አካሉ ሰማያዊ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታነህ ባልቻ የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ጥቅምት 26 ቀን 2010 ዓ.ም ባደረጉት የጋራ ምክክር ሰማያዊ ፓርቲን በአባልነት ለመቀላቀል መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

የቀድሞ የአንድነት ለዲሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀል ሰላማዊ ትግሉን ወደፊት ያስኬደዋል!!

የሰማያዊ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰኞ ጥቅምት 27/2010 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራሮች እና አባላት የወሰኑትን እጅግ ብስለት የተሞላበት ውሳኔ በማድነቅ ውሳኔያቸው ለሕባችን የተሻለ አማራጭ ይዞ መቅረብን የሚያስችል መሆኑን በመተማመኑ በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀፅ 5 ንዑስ አንቀፅ 2/3 መሰረት የእጩ አባልነት ጊዜያቸውን ሳይጠብቁ በሙሉ አባልነት ፓርቲውን እንዲቀላቀሉ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ ከዚህ ቀደምም በ2007 ዓ.ም የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራሮችን እና አባላትን በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት በሙሉ አባልነት ተቀብሎ የነበረ ሲሆን እኒሁ አባላት እና አመራሮች በፓርቲው መዋቅር ውስጥ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሰላማዊ ትግሉን እየመሩ ይገኛሉ፡፡

የሰማያዊ እና አረና ትግራይ ፓርቲዎች የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ

የሰማያዊ እና አረና ትግራይ ፓርቲዎች በሳምንቱ መጨረሻ ተከታታይ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸዉን ለዶቼ ቬለ ገለፁ። እንዲያም ሆኖ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፉ እዉቅና እንደተነፈገ አመልክቷል። አረና በበኩሉ ከሚመለከተዉ አካል ምላሽ እየጠበቀ ነዉ።

http://www.dw.com/am/%E1%8B%A8%E1%88%B0%E1%88%9B%E1%8B%AB%E1%8B%8A-%E1%8...

መንግሥት ለሕዝቡ ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ ሰማያዊ ፓርቲ ጠየቀ

መንግስት ጣቱን ከጠበንጃ ቃታ ላይ አንስቶ ለሕዝቡ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ይስጥ ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ጠየቀ። ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግም ስልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክብ አሳሰበ።
አዲስ አበባ —
መንግስት ጣቱን ከጠበንጃ ቃታ ላይ አንስቶ ለሕዝቡ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ይስጥ ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ጠየቀ። ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግም ስልጣኑን ለሕዝብ እንዲያስረክብ አሳሰበ።

ፓርቲው በመጭው ዕሁድ በዚህ ጉዳይ ላይ ከሕዝብ ጋር እመክራለሁ ሲልም የአዳራሻ ውስጥ ስብሰባ ማዘጋጀቱንም አስታወቀ።

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ ከቀትር በኋላ በጠራው ጋዜጣዊ ጉባዔ ላይ ያሰራጨው የጽሑፍ መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አምባገነናዊ ሥርዓቱ ስለአንገሸገሸው ሥርዓቱን ለማውገዝና ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቱን ለማስከበር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የአደባባይ ተቃውሞ እያሰማ እንደሆነ ያስረዳል፡፡

ታጋዮችን በማሠር የሕዝብን ጥያቄ ማቆም አይቻልም!

ታጋዮችን በማሠር የሕዝብን ጥያቄ ማቆም አይቻልም!
ሰማያዊ ፓርቲ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ለለውጥ ቁርጠኛ አቋም ያላቸውን ወጣት ፖለቲከኞች ያፈራ የፖለቲካ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ፓርቲው የሚደርስበትን ጫናና ፈተና ተቋቁሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ እውነተኛ የሥልጣን ባለቤት እንዲሆን በፅኑ እየታገለም ይገኛል፡፡
ሆኖም ገዥው ፓርቲ በእያንዳንዱ የፓርቲው እንቅስቃሴ ውስጥ ጣልቃ በመግባት አመራርና አባላቱን እያፈሠ ወደ እስር ቤት መወርወሩ የተለመደ ተግባሩ ሆኗል፡፡ ሕዝብ መብቱን እንዲያውቅና እንዲጠይቅ ፓርቲያችን የሚያደርጋቸውን የአዳራሽና የአደባባይ ስብሰባዎች ህገ-መንግሥቱን በመጣስ በህገ-ወጥ መንገድ ከማፈኑም በተጨማሪ የፈጠራ ክስ እየፈበረከ በሰላማዊ መንገድ በድፍረትና በቆራጥነት የሚታገሉ አባላቶቻችንን ማሰርና ማንገላታቱን ዛሬም አባብሶ ቀጥሎበታል፡፡

የመግባባት ዴሞክራሲ ገላጭ ምስሎቸ--በዶ/ር አድማሱ ገበየሁ

4.1 አገር እንደ ቤተሰብ

ብዙ ጊዜ በኅብረተሰብ ውስጥ ስላሉ አስተዳደራዊ ተቋሞች ሲታሰብ በሰዎች አእምሮ የሚብላላው ከቤተሰብ

ሕይዎትን በአምሳያነት በመቃኘት ነው። አገርንና አስተዳደርን በተመለከተ መመሳሰልን ለማመልከት የሚጠቀሰው

“አገር እንደ ቤተሰብ” እና “አገር አስተዳደርን እንደ ልጅ-አስተዳደግ” በአምሳያነት በማቆራኘት ነው።

በአእምሯችን ውስጥ ስለ ቤተሰብ የተቀረፀው እይታ በፖለቲካ እምነታችን ላይ ተጽእኖ ማሳረፉ የአጋጣሚ ጉዳይ

አይደለም። ገና ስንወለድ ጀምሮ አስተዳደራዊ ልምድ የምናገኘው ከቤተሰብ ነው። ወላጆቻችን “ያስተዳድሩናል”፤

አቅማቸው በፈቀደ መጠን፡- ከመጥፎ ነገር ይጠብቁናል፤ ምን ማድረግ አንደምንችልና እንደማንችል ይነግሩናል፤

በቂ አቅርቦት እንዳለን ያረጋግጡጥልናል፤ ያስተምሩናል፤ እና እኛም የቤተሰቡ አኗኗር እንዲሰምር የተቻለንን ያህል

አስተዋጽኦ እንድናደርግ አመራር ይሰጣሉ።

ሰማያዊ እና መኢአድ አብሮ ለመስራት የትብብር ሰነድ ተፈራረሙ።

ሰማያዊ እና መኢአድ አብሮ ለመስራት የትብብር ሰነድ ተፈራረሙ።
ስለትብብሩ አጭር ማብራሪያ ቀርቧል

በነፃና ገለልተኛ አደራዳሪ ያልተመራ ድርድር ለህዝብ ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ አያመጣም!

ገዥው ፓርቲ ግንቦት 2007 ዓ.ም. በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ መቶ በመቶ ድልን ተጐናፅፌያለሁ ብሎ አውጆ መስከረም 2008 ዓ.ም. መንግሥት ቢመሰርትም ጥቂት ወራትን እንኳን በሰላም ማስተዳደር አቅቶት ሀገሪቱ በተቃውሞ መታመስ ጀመረች፡፡

የኖርዌይ አምባሳደር ከሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጋር ውይይት አካሄዱ !

Norwegian Embassy in Addis baba

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ እንዲሁም የፓርቲው የውጪ ጉዳይ ኃላፊ መምህር አበበ አካሉ፤ የኖርዊይ አምባሳደር ባደረጉላቸው ጥሪ መሰረት ከአምባሳደር አንድሪያስ እና ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር በኖርዌይ ኢምባሲ ውይይት አካሄዱ ።

የሰማያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዋቀሩ!

መስከረም 28 ቀን 2009 በተከናወነ ጠቅላላ ጉባዔ የሰማያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዋቀሩ፡፡
ፕሬዚዳንቱ አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴያቸውን ጥቅምት 13 ቀን 2009 ዓ.ም. በተካሄደ የፓርቲው ስብሰባ ለፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት አቅርበው አፀድቀዋል፡፡
በዚህም መሠረት :
- ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ - ምክትል ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊ፣
- ኢንጂነር ስሜነህ ፀሐይ የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ፣
- አቶ ሰሎሞን ተሰማ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣
- አቶ አበበ አካሉ የውጭ ግንኙነት ኃላፊ፣
- አቶ ነአሮን ሰይፉ የጥናትና ስትራቴጂ ኃላፊ፣
- ወ/ሮ ቅድስት አሰበ የሕግ ጉዳይ ኃላፊ፣
- አቶ ሰዒድ ኢብራሒም የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ፣
- ኢንጂነር ዳዊት ዋለልኝ የአባላት መረጃና ደኅንነት ኃላፊ፣
- ወ/ሪት ብሌን መስፍን የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ፣

Pages

Subscribe to semayawiparty RSS