You are here

የመግባባት ዴሞክራሲ ገላጭ ምስሎቸ--በዶ/ር አድማሱ ገበየሁ

4.1 አገር እንደ ቤተሰብ

ብዙ ጊዜ በኅብረተሰብ ውስጥ ስላሉ አስተዳደራዊ ተቋሞች ሲታሰብ በሰዎች አእምሮ የሚብላላው ከቤተሰብ

ሕይዎትን በአምሳያነት በመቃኘት ነው። አገርንና አስተዳደርን በተመለከተ መመሳሰልን ለማመልከት የሚጠቀሰው

“አገር እንደ ቤተሰብ” እና “አገር አስተዳደርን እንደ ልጅ-አስተዳደግ” በአምሳያነት በማቆራኘት ነው።

በአእምሯችን ውስጥ ስለ ቤተሰብ የተቀረፀው እይታ በፖለቲካ እምነታችን ላይ ተጽእኖ ማሳረፉ የአጋጣሚ ጉዳይ

አይደለም። ገና ስንወለድ ጀምሮ አስተዳደራዊ ልምድ የምናገኘው ከቤተሰብ ነው። ወላጆቻችን “ያስተዳድሩናል”፤

አቅማቸው በፈቀደ መጠን፡- ከመጥፎ ነገር ይጠብቁናል፤ ምን ማድረግ አንደምንችልና እንደማንችል ይነግሩናል፤

በቂ አቅርቦት እንዳለን ያረጋግጡጥልናል፤ ያስተምሩናል፤ እና እኛም የቤተሰቡ አኗኗር እንዲሰምር የተቻለንን ያህል

አስተዋጽኦ እንድናደርግ አመራር ይሰጣሉ።

ስለዚህ ነው አገርን በቤተሰብ ጋር የምንመስለው፤ ስለዚህ ነው እናት አገር ኢትዮጵያ የምንለው። አገርን በቤተሰብ

ስንመስል የሚፈጠረው ስሜት የፓለቲካዊ ምልከታችን ምንጭ ነው። ሀገርን በቤተሰብ መመሰል ተገቢ መሆኑንና

በርካታ ጥናቶች አረጋግጠዋል። አገር እንደ ቤት፣ ዜግነት እንደ ቤተሰብ አባልነት፣ የመንግሥት አመራሮች አንደ

ወላጆች (እማወራና አባወራ) ይመሰላሉ። መንግሥት ለዜጎች ያለበት ኃላፊነት፣ ወላጆች ለልጆቻቸው ባለባቸው

ኃላፊነት ይመሰላል። ለደህንነት ዋስትና መስጠት፣ (ከክፉ ነገር ይጠብቁናል)፣ ሕግ ማውጣት፣ (ምን ማድረግ

እንምንችልና ምን ማድረግ እንደሌለብን ይነግሩናል፣)፤ ኢኮኖሚን መምራት፣ (የሚያስፈልገን አቅርቦት እንዲሟላ

ይጥራሉ፣)፤ ትምህርት ለሁሉም ማዳረስ፣ (ያስተምሩናል፣)።

ግን መንግሥትና ቤተሰብ የሚለያዩበት አንድ ጉዳይ አለ አለ። አንድ በተወሰነ ወቅት የሚገኝን ዓመታዊ ገቢን ከወር

አስከ ወር፡ ከሳምንት አስከ ሳምንት፡ የቀኑንም ለሰዓቶች እንደ እናቶቻችን አብቃቅቶ መጥኖና አመጣጥኖ ማቅረብ

የሚችል የበጀት ሊቃውንት ወይም ተቋማት በየትም አገር ያለ መንግሥት ኖሮት የሚያውቅ አይመስለኝም።

በዓለማችን ሁለት ዓይነት የቤተሰብ ሞደሎች አሉ። አንደኛው “ጥብቅ-አባት ሞዴል” የሚባለው ሲሆን “ወግ-

አጥባቂ” ከሚባለው ፖለቲካዊ ርዕዮተ-ዓለም ጋር ይመሳሰላል። ሁለተኛው “ተንከባካቢ-ወላጅ ሞዴል” የሚባለው

ሲሆን “ተራማጅ” ከሚባለው ፖለቲካዊ ርዕዮተ-ዓለም ጋር ይመሳሰላል።

ይህ በቤተሰብ ላይ የተመሠረተ አስተሳሰብ ሁለት እርስ-በርሳቸው የሚቃረኑ ግብረ-ገብነት ሥርዓት ላይ

የተመሠረተ፡ አገርን የማስተዳደር ውጥረት ፈጥሯል። እነዚህ ሁለት ርእዮተ-ዓለሞች አገሮች አንደት

አንደሚስተዳደሩ ብቻ ሳይሆን በበርካታ መንገዶች የዜጎችም አኗኗር ምን መምሰል እንዳለበት ይወስናል።

ሁለቱ ሞዴሎች እርስ በርሳቸው ይፃረራሉ። ሁለቱን ሞዴሎች በተመሳሳይ ሁኔታ፣ በተመሳሳይ ጊዜ፣ በአንድ ሰው

ተግባራዊ ማድረግ አይቻልም። ሁለቱ ሞዴሎች እርስ በርሳቸው አይጣጣሙም። ይህ የግብረ-ገብነት ፖለቲካ

2

ሞዴል አመለካከት ውጤት ነው። የግብረ-ገብነት ፖለቲካ ሞዴል ፖለቲካዊ ራዕይን በተሟላ-ተራማጅነትና

በተሟላ-ወግ-አጥባቂነት ይመድባል። ሁለቱን የሚያቀራርብ አመለካከት እንደ ብልሽት ወይም ብርዝ ወይም እንደ

ዝቅተኛ ጥራት ይታያል።

ወግ-አጥባቂዎችና ተራማጆች በበርካታ መሠረታዊ ፖለቲካዊ ጽንሰ-ሃሳቦች ማለትም ፍትሃዊነት፡ ነፃነት፡ እኩልነት፡

ደህንነት፡ ወዘተ. በመሳሰሉት ትርጉም ላይ ልዩነት አላቸው። እነዚህ ጉዳዮች ደግሞ ለዜጎች ፖለቲካዊ ሕይዎት

አሳሳቢ ናቸው።

ከዚህ ቀጥሎ የጥብቅ-አባት ሞዴልን የሚከተል ቤተሰቦችና የተንከባካቢ-ወላጅ ሞዴልን የሚከተሉ ወላጆች

በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያላቸው አመለካከቶች ቀርቧል። በሁለቱ መካከል ሊመደቡ የሚችሉ ከሁለቱም በተለያየ

መጠን የተቀየጡ ሌሎች የቤተሰብ ሞደሎች ሊኖሩ ቢችሉም በዚህ ምእራፍ ትኩረት የተሰጠው የተሟሉ (ፍፁማዊ)

የሆኑትን የጥብቅ-አባት ሞዴል እና የተንከባካቢ ሞዴል ላይ ብቻ ነው።

4.2 የጥብቅ-አባት ሞዴል

በቤተሰብ ሁለት ወላጆች አሉ፤ አባትና እናት። የጥብቅ አባት ሞዴል ተከታይ ቤተሰቦች አኗኗራቸው ፉክክር ሂደት

ውስጥ ያለ የማሸነፍና የመሸነፍ ውጤትን የሚያስከትል አደገኛ ዓለም ውስጥ ነው ብለው ያምናሉ። በመሆኑም

በአደገኛው ዓለም ውስጥ ያሉትን ፈተናዎችና ውድድሮች በድል አድራጊነት ወይም በአሸናፊነት የሚወጣና ቤተሰቡን

የሚጠብቅና ከአደጋ የሚከላከል ጠንካራ አባት (አባወራ) ያስፈልጋል።

በግብረ-ገብነት መመዘኛ መሠረት ያሉት ፍፁም-ትክክል እና ፍፁም-ስህተት ናቸው። ጥብቅ-አባት የቤተሰቡ የግብረ-

ገብነት ባለሥልጣን ነው። ትክክልና ስህተትን የሚያውቀው እሱ በመሆኑ የቤተሰቡም ባለሥልጣን እሱ ነው።

የአባት ሥልጣን ለጥያቄ አይቀርብም። ለአባት ታዛዥ መሆን ሕጋዊነት የሚመነጨው አባት ካለው ግብረ-ገብነት

ጋር ከተያያዘ ሥልጣን ነው።

እናት ለአባት ሥልጣን ድጋፍ ትሰጣለች። ይሁን እንጂ ቤተሰብ በአባት ሥልጣን አጠቃቀም ምክኒያት ጉዳት

እንዳይደርስበት ለመከላከል የሚያስችል ከግብረ-ገብነት የሚመነጭ የራሷ ሕጋዊ አቅም የላትም። እናት ለልጆቿ

የምታደርጋቸው ነገሮች አሉ። ፍቅር መስጠት፡ ስለእነሱ ማሰብና መጨነቅ፡ ምክር መስጠት፡ ማጽናናት፡ በተቀጡም

ጊዜ ከሥቃያቸው እንዲያገግሙ ማባበል የመሳሰሉትን ታከናውናለች።

ልጆች የሚወለዱት ያለ ሥነ-ሥርዓት ነው። አባት ክፉን ከደጉ እንዲለዩ፣ ሥነ-ሥርዓት እንዲያውቁ ያስምራቸዋል።

ልጆች ትእዛዝ ሲጥሱ ይቀጣሉ፤ ልጆችን ከቅጣት የሚድኑት አባታቸውን የሚያስተምራቸውን በግብረ-ገብነት የታነፀ

ሥነ-ሥርዓት ከከበሩ ብቻ ነው። ይህን እንድያደርጉም ልዩ ልዩ ማበረታቻ ይመቻችላቸዋል። ይህ “ጠጣር ፍቅር”

ግብረ-ገብነትን ለማስተማር የሚበጅ ብቸኛ መንገድ ተደርጎ ይታያል። በዚህ መንገድ ያደጉ ልጆች ይህንኑ አሠራ

ፍላጎታቸውን ለማሟላት፣ የገባያ ውድድር ለማሸነፍና የሀብት ክምችታቸው የላቀ እንዲሆን ይጠቀሙበታል።

የጥብቅ-አባት ሞዴል 30 ክፍልፋዮች ሲኖሩት፣ ዝርዝራቸውና ይዘታቸው ከዚህ በታች ቀርቧል። የሞዴሉ

ክፍልፋዮች፡ (ሀ) የግረገብነት ባህሪይ መለያዎች፣ (ለ) የልጅ-አስተዳደግ ግብረ-ገብነት፣ እና (ሐ) የሕፃን ተፈጥሮ

እና ርዕዮተ-ዓለም እምነት፣በሚባሉ ምድቦች ተፈርጀዋል። ከያንዳንዱ ክፍልፋይ ጋር በተያያዘ የጥብቅ-አባት

ሞዴልን የሚከተሉ ሰዎች እንከን-የለሽ (ፍፁም የሆነ) የቤተሰብ ሕይዎት እንደሚገኝ የሚሰጡትን ምክኒያት በውል

ለመረዳት የሚያግዙ ገለጻዎችና ምሳሌዎች ተካተዋል።።

(ሀ) የግረገብነት ባህሪይ መለያዎች

የጥብቅ-አባት ሞዴል፡ ራስን መቆጣጠር፣ ራስን መቻል፣ ታዛዢነት፣ ከራስ ወገን ጋር ብቻ መተሳሰብ፣ ተራት፣

የተለመደ አሠራን መከተል፣ የፆታ ሚና፤ የማፈንገጥ ነውርነት፤ እና የመታገዝ ነውርነት፤ የሚባሉ የግረገብነት ባህሪይ

መለያዎችን ያካትታል። ይህን በተመለከተ በምሳሌዎች የታገዙ አጫጭር መግለጣዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።

(1) ራስን መቆጣጠር፡- ራስን መቆጣጠር የግብረ-ገብነት ምልክት ነው። ስለሆነም ወላጆች ልጆቻቸው ራሳቸውን

እንዲቆጣጠሩ ማስተማር አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ልጆች ከሕፃንነታቸው ጀምረው “ስቃይ የለም፣ ትርፍ የለም”

የሚለውን አባባል መንፈስ ሊረዱት ይገባል።)

3

(2) ራስን መቻል፡- በአስተማማኝ ደረጃ ራስን መቻል የግብረ-ገብነትና የማኅበራዊ ግንኙነት ልዕልና ባህርይ ነው።

በአስተማማኝ ደረጃ ሁሉም ራሱን ከቻለ ህብረተሰቡ በአጠቃላይ የተሻለ ደረጃ ላ ይደርሳል። በተቻለ መጠን፡

ልጆች ገና ከሕፃንነታቸው ጀምሮ በራሳቸው ላይ እንዴት እንዲመኩ መማር አለባቸው ። (ለምሳሌ፡- ምንም እንኳን

ወላጆች ልጆቻቸውን ለመደገፍ በቂ ገንዘብ ቢኖራቸው፣ በተቻለ መጠን፡ ልጆች ገና ከሕፃንነታቸው ጀምሮ

የራሳቸው ገንዘብ ባለቤት መሆን አለባቸው።)

(3) ታዛዢነት፡- ታዛዢነት ግብረ-ገብነት ነው። በላጆች ልጆቻቸውን የባለሥልጣንን ትእዛዝ መፈፀም እንዳለባቸው

ማስተማር አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ያለመታዘዝ ሁኔታ እያዩ በችልታ ማለፍ የለባቸውም።

ወላጆች እንደዚህ ዓይነት ድርጊት ፈጽሞ ሊታገሱት አይገባም።)

(4) ከራስ ወገን ጋር ብቻ መተሳሰብ፡- ከራስ ወገን ጋር ብቻ መተሳሰብ ግብረ-ገብነት ነው። ነገር ግን ከሌሎች

ወገኖች ጋር መተሳሰብና መረዳዳት ፈጽሞ ስህተት ነው። (ለምሳሌ፡- የሌሎች ሰዎች ጉዳይ እኛ አይመለከተንም፣

እኛን ሊያሳስበን አይገባም። ነገር ግን ቤተሰብን በተመለከተ፡ አንዱ የቤተሰብ አባል ሌላውን የቤተሰብ አባል

መጠበቅ አለበት፣ የአንዱ አባል ችግር ችግር፡ የሁሉም አባሎች ችግር ነው።)

(5) ጥራት፡- የአካላዊና መንፈሳዊ ጥራት የመልካም ግብረ-ገብነት ምልክቶች ናቸው። (ለምሳሌ፡- ልጅች ያልጠራ

ሃሳብን እንደት እንደሚያስወግዱ መማር አለባቸው።)

(6) የተለመደ አሠራን መከተል፡- የተለመደ አሠራን መከተል ግብረ-ገብነት ነው። ወላጆች ልማዳዊና ባህላዊ

አሠራሮችን ለልጆቻቸው ማስተማር አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ወላጆች ለልጆቻው ጥሩ ምሳሌዎች መሆን አለባቸው።

ስለሆነም፡ ወላጆች ባህላዊ አኗኗርን ሳያዛንፉና ሳያጓድሉ መከተል አለባቸው።)

(7) የፆታ ሚና፡- የወንዶችና የሴቶች ተፈጥሮ የተለያየ በመሆኑ በኅብረተሰብ ውስጥ የተለያየ ባህላዊ ሚና አላቸው።

ስለዚህ ወላጆች ባህሉ የሚፈቅደውን የፆታ ሚና መከተል አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ሴቶች ልጆች በቤት ውስጥ ሥራ

መሳተፍ አለባቸው። ወንዶች ልጆች ደግሞ በወንዶች ተግባር መሠማራት አለባቸው። ሴቶች ልጆች ለወንዶች

የተመደበውን ሥራ መሥራት፣ ወንዶች ልጆች ደግሞ በለቶች የተመደበውን ሥራ መሥራት፣ ነውር ነው።)

(8) የማፈንገጥ ነውርነት፡- ማፈንገጥ ግብረ-ገብነት አይደለም፣ ነውር ነው። ማፈንገጥ ራስን ለመቆጣጠር እንቅፋት

ነው። (ለምሳሌ፡- እንዲያፈነግጡ የሚፈቀድላቸው ልጆች ምንጊዜም ቁም ነገረኛና ስኬታማ ሊሆኑ አይችሉም።)

(9) የመታገዝ ነውርነት፡- የሌሎች ሰዎችን እርዳታ መጠየቅ ከግብረ-ገብነት ውጭ ነው። ኃላፊነት የሚሰማው ልጅ፡

ምንም ቢቸገር የሌሎችን እርዳታ ፈጽሞ አይጠይቅም፤ ምንጊዜም የራሱን ችግር በራሱ ማሸነፍ አለበት፤ እራሱን

መቻል አለበት። (ለምሳሌ፡- ልጆችን ስለ ኃላፊነት ማስተማር ማለት በራሳቸው ተማምነው የራሳቸውን እንዲችሉ

አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ማለት ነው መቻል ማለት ነው።)

(ለ) የልጅ-አስተዳደግ ግብረ-ገብነት

የጥብቅ-አባት ሞዴል፡ ደንብን ማክበርና ማስከበር፤ ልጅን በሥርዓት ማሳደግ፤ ተዋረድን የጠበቀ የሃሳብ ልውውጥ፤

የወላጆች ባለ ሙሉ ሥልጣንነት፤ የጥብቅ ቁጥጥር አስፈላጊት፣ የግብረ-ገብነት ጥንካሬ (መጋፈጥ)፣ የቅጣትና

የሽልማት አስፈላጊነት፣ ውድድር (ፉክክር)፣ አፀፋ መመለስ፣ የሚገባን ማግኘት፣ ጥብቅነት፣ ወላጆች መወላወልና

ማቅማማት የለባቸውም፤ እናመላላትና መታገስ ነውር ነው፣ የሚባሉ የልጅ-አስተዳደግ ግብረ-ገብነት መገለጫዎች

ያካትታል። ይህን በተመለከተ በምሳሌዎች የታገዙ አጫጭር መግለጣዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።

(10) ደንብን ማክበርና ማስከበር፡- ወላጆች ግብረ-ገብነትን በተመለከተ ጥብቅ የሆኑ ደንቦች መቅረጽ አለባቸው፤

በትክክል መፈጸማቸውን ማረጋገጥ አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ያለማዛነፍ በጥብቅ ደንብን ማስከበርና ማክበር የልጅ-

አስተዳደግ ዋና መሠረት ነገር ነው።)

(11) ልጅን በሥርዓት ማሳደግ፡-: መልካም የልጅ-አስተዳደግ ልጆችን መቅረጽ ነው። ልጆች ሲወለዱ ጥሩነት

ስለሚጎድላቸው፣ በወላጆች ጥረት ወደ ጥሩነት መለወጥ አለባቸው። ልጆች ግብረ-ገብነት እንዲኖራቸው ለማድረግ፣

ወላጆች ሁልጊዜ በልጆች አስተሳሰብና ባህርይ ጣልቃ መግባት አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ልጆች ከተለመደው ውጭ

4

የሆነ ባህርይ ማሳየት ሲጀምሩ፣ ወላጆች በፍጥነት ጣልቃ ገብተው ትክለኛው አስተሳሰብና አሠራር ተመልሶ በልጆች

አእምሮ ውስጥ ቦታውን እንዲዝ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።)

(12) ተዋረድን የጠበቀ የሃሳብ ልውውጥ፡- በቤተሰብ አባሎች መካከል የሚደረግ የሃሳብ ልውውጥ ተዋረድን የጠበቀ

መሆን አለበት። ወላጆች በሚሰጡት ውሳኔ የልጆች ተሳትፎ አስፈላጊ አይደለም። (ለምሳሌ፡- ልጆች ምን ጊዜም

ቢሆን ወላጆቻቸው በሚሰጡት ውሳኔ ላይ የማሻሻያ ሃሳብም ሆነ ጥያቄ ማቅረብ የለባቸውም።)

(13) የወላጆች ባለ ሙሉ ሥልጣንነት፡- ምን ጊዜም ቢሆን ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ገደብ የሌለው ሥልጣን

አላቸው። (ለምሳሌ፡- ወላጆች የአመጽ አዝማሚያ የሚያሳይን ልጅ በቅጣት መግራት አለባቸው።)

(14) የጥብቅ ቁጥጥር አስፈላጊት፡- ወላጆች በልጆቻቸው ሕይዎት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው። ወላጆች

ልጆቻቸውን ለመቆጣጠር የሚገድባቸው ነገር መኖር የለበትም፤ ይህንንም ለማረጋገጥ የልጆቸውን ግለኝነት የጣሰ

ብርበራ ማካሄድም ይችላሉ። (ለምሳሌ፡- ልጆች ከወላጆቻቸው የሚደብቁት ሚስጥር የለበትም።)

(15) የግብረ-ገብነት ጥንካሬ (መጋፈጥ)፡- ልጆች የሚያድጉትና የሚጠነክሩት፣ ቅጣትን ሲቀበሉ፡ ፈተናን ሲወጡ፡

እና ስቃይን ሲለምዱ ነው። (ለምሳሌ፡- ልጆች ምንም ያህል መከራ፡ ጭንቅና ሥቃይ ቢደርስባቸው፣ አልቃሻ ሆነው

መታየት የለባቸውም።)

(16) የቅጣትና የሽልማት አስፈላጊነት፡- ወላጆች ልጆቻቸውን የመቅጣት ኃላፊነት አለባቸው፤ ልጆች ግብረ-ገብነት

እንዲኖራቸው ልጆች ባጠፉ ጊዜ መቀጣት አለባቸው። እንደዚሁም ግብረ-ገብነት ያለው ተግባር ከፈጸሙ መሸለም

አለባቸው፣ ልጆች ሽልማት ካገኙ ብርቱ፡ ጠንካራና አሸናፊ ለመሆን ያበረታታቸዋል። (ለምሳሌ፡- የወላጆች

አካላዊም ይሁን መንፈሳዊ ቅጣት ልጆች ሥነ-ሥርዓት እንዲኖራቸው ያደርጋል። እንደዚሁም ወላጆች ለልጆቻው

የሚሰጡት የገንዘብ ሽልማት ልጆችን ብርቱና ጠንካራ ተፎካካሪ እንዲሆኑ ማበረታቻ ይሆናቸዋል።)

(17) ውድድር (ፉክክር)፡- ውድድር ልጆችን ጠንካራ ያደርጋል፤ በመሆኑም ወላጆች ልጆቻቸው ከሌሎች ጋር

ተወዳድሮ የማሸነፍ የመወዳደር ብቃት እንዲኖራቸው ተገቢ ትምህርት መስጠት አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ልጆች

ሲጫዎቱ ግባቸው ለማሸነፍ መሆን አለበት።)

(18) አፀፋ መመለስ፡- ግብረ-ገብነት የጎደለው ባህርይ አፀፋ በመመለስ ይስተካከላል። ይህ ማለት ከባድ ጥፋት

በከባድ ቅጣት ይስተካከላል ማለት ነው። (ለምሳሌ፡- አንድ ልጅ ሌላውን ቢመታው፣ የተመታው መልሶ የመታውን

ቢመታ ትክክለኛ ምላሽ ይሆናል።)

(19) የሚገባን ማግኘት፡- ፍትሃዊ ማለት ሁልጊዜ ልጆች ማግኜት የሚገባቸው ነገር ድርጊታቸው ከሚያስገኘው

ውጤት ጋር የተመጣጠነ መሆን አለበት። (ለምሳሌ፡- ወላጆች ለልጆች የሚያደርጉት ነገር ልጆች በግብረ-ገብነት

ሚዛን ከሚያገኙት ውጤት ጋር መመጣጠን አለበት።)

(20) ጥብቅነት፡- ፍፁማዊ እንክብካቤ ማለት “ትብቅ ፍቅር” ማለት ነው። ወላጆች ለልጆቻቸው ሲሉ ልጆቻቸው

ጥብቅ ሥነ-ሥርዓት እንዲኖራቸው ማድረግ አለባቸው። ጥብቅነት የወላጅነት ፍቅር መግለጫ ነው። (ለምሳሌ፡-

እጅን ጠበቅ አድርጎ መጨበጥ ወይም ትከሻን ጠበቅ አድርጎ ማቀፍ የወላጅት ፍቅር መግለጫ ነው።)

(21) ወላጆች መወላወልና ማቅማማት የለባቸውም፡- ወላጆች በሚሰጡት ትእዛዝም ሆነ ውሳኔ የመወላወልና

የማቅማማት ስሜት ማሳት በልጆች ላይ የባሀርና የግብረ-ገብነት ድክመት ይፈጥራል። (ለምሳሌ፡- ወላጆች

ለልጆቻቸው የሚሰጡት አማራጭ ሁለት ብቻ መሆን አለበት። ውሰድ ወይም ተወው፡ ስቀል ወይም አውርድ፣

ውጣ ወይም ግባ፡ ወዘተ. መሆን አለበት።)

(22) መላላትና መታገስ ነውር ነው፡- ወላጆች ፈጽሞ ልጆቻቸውን ከመቅጣት መዘናጋት የለባቸውም።

የሚያጠራጥር ነገር ሲያጋጥም፡ ከመላላትና ከመታገስ ይልቅ ሥልጣንን ከመጠቀም በኩል መሆን ይሻላል። ጥርጣሬ

ከተፈጠረ፡ ያላጠፋ ልጅ ቢቀጣ ይሻላል፣ ያጠፋ ልጅ ከቅጣት ከሚያመልጥ። (ለምሳሌ፡- የልጆችን መጥፎ ባህርይ

ለማረም ከተፈለገ፡ ቅጣትን ከማቅለልና ከማሳነስ ይልቅ ቅጣትን ማክበድና ማበርከት ይሻላል።)

(ሐ) የሕፃን ተፈጥሮ እና ርዕዮተ-ዓለም

5

በጥብቅ-አባት ሞዴል ይዘት ውስጥ የተካተቱት የግረገብነት ባህሪይ መለያዎች፣ የልጅ-አስተዳደግ ግብረ-ገብነት

ከየሕፃን ተፈጥሮ እና ዓለማዊ እምነት ጋር በጥብቅ የተሳሰሩ ናቸው። ድርጊቶችና ቀጥተኛ ውጤታቸው፣ የጥሩና

የመጥፎ ጥንድነት፤ የግብረ-ገብነት መንፈስ፣ መጥፎ ጠባይን ማጋባት፣ የግብረገብነት እርከኖች፣ የወንዶች

የበላይነት፣ ፍፁማዊ የሆነ ማኅበራዊ ሥልጣን፣ እና ሥርዓትን መጠበቅ፣ የሚባሉ የሕፃን ተፈጥሮ እና ዓለማዊ

እምነት መገለጫዎች ያካትታል። ይህን በተመለከተ በምሳሌዎች የታገዙ አጫጭር መግለጣዎች እንደሚከተለው

ቀርበዋል።

(23) ድርጊቶችና ቀጥተኛ ውጤታቸው: በዓለም ውስጥ የተከሰቱ ክንውኖች ቀጥተኛ ምክኒያት አላቸው። በመሆኑም

የአንድ ሰው ውድቀት በሰውየው በራሱ ድክመት የተፈጠረ ነው። (ለምሳሌ፡- ልጆች ቢሳካላቸው የራሳቸው ጥረት

ውጤት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ልጆች ቢወድቁ የራሳቸው ጥፋት ውጤት ነው።)

(24) የጥሩና የመጥፎ ጥንድነት፡- ዓለም በመጥፎና በጥሩ ይከፈላል። (ለምሳሌ፡- ዓለም ውስጥ መጥፎና ጥሩ አንድ

ላይ የሚገኙ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጾች ናቸው።)

(25) የግብረ-ገብነት መንፈስ፡- የአንድ ሰው ባህርይ የግብረ-ገብነት መንፈስ መገለጫ ነው። ጥሩ ነገር የሚሠሩ ሰዎች

ጥሩ መንፈስ አላቸው። በሌላ በኩል ደግሞ መጥፎ ነገር የሚሠሩ ሰዎች መጥፎ መንፈስ አላቸው። የአንድ ሰው

የግብረ-ገብነት መንፈስ ሊለወጥ አይችልም። (ለምሳሌ፡- ሁልጊዜ መጥፎ ነገር የሚሠራ ሰው ሊለወጥ አይችልም፤

እንደዚህ ያለ ሰው ከልቡ መጥፎ ነው።)

(26) መጥፎ ጠባይን ማጋባት፡- ግብረ-ገብነት የሌለው ባህርይ ከአንድ ግለሰብ ወደ ሌላ ግለሰብ የሚተላለፍ በሽታ

ነው። በመሆኑም ግብረ-ገብነት ያላቸው ሰዎች ግብረ-ገብነት ከሌላቸው ሰዎች መራቅ አለባቸው። (ለምሳሌ፡- መጥፎ

ነገር ከአንድ ሰው ወደ ሌላ የሚጋባ ነው። ስለዚህ ግብረ-ገብነት ያላቸው ልጆች ከመጥፎ ልጆች ጋር ማኅበራዊ

ግንኙነት መፍጠር አደገኛ ነው።)

(27) የግብረ-ገብነት እርከኖች፡- በዓለም ውስጥ ተፈጥሯዊ የሆኑ የግብረ-ገብነት እርከኖች አሉ፤ ፈጣሪ ከሰዎች

በላይ ነው፤ ሰው ከሌሎች ፍጡሮች በላይ ነው፤ ወንዶች ከሴቶች በላይ ናቸው። (ለምሳሌ፡- ልጆች ተፈጥሯዊ

የሆነውን የግብረ-ገብነት እርከን በጥንቃቄ መማር አለባቸው።)

(28) የወንዶች የበላይነት፡- ወንዶች በሴቶች ላይ ተፈጥሯዊ የሆነ ሥልጣን አላቸው። ስለሆነም ወንዶች የቤተሰብ

ከፍተኛውን የሥልጣን ደረጃ መያዝ አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ሥነ-ሥርዓት በተጠበቀበት ቤተሰብ ውሳኔ የመስጠት

ሥልጣን የአባት ነው።)

(29) ፍፁማዊ የሆነ ማኅበራዊ ሥልጣን፡- በመሠረቱ ጥብቅ-አባቶች ግብረ-ገብነት አላቸው። ስለሆነም

ቤተሰቦቻቸውን በተመለከተ ከውጭ ባለሥልጣኖች ጣልቃ ገብነት የተጠበቀ ሙሉ ሥልጣን አላቸው። (ለምሳሌ፡

- በቤተሰብ ጉዳይን በተመለከተ ከቤተሰብ አባላት ውጭ የሆኑ ሰዎች ጣልቃ ሊገቡ አይችሉም።)

(30) ሥርዓትን መጠበቅ፡- ጥብቅ-አባት ግብረ-ገብነት ያለ ምንም ጥርጥር ትክክለኛ ነው። ስለዚህ በሌሎች ግብረ-

ገብነት ሥርዓቶች እንዳይገፋና እንዳይጠቃ ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል። (ለምሳሌ፡- የጥብቅ-አባት ግብረ-ገብነት

ተከታዮች ልጆቻቸውን ከሌላ ዓይነት ግብረ-ገብነት ተከታይ አዋቂ ሰዎች ጋር እንዳይገናኙ ማድረግ አለባቸው።)

4.3 የተንከባካቢ-ወላጅ ሞዴል

በዚህ ሞዴል መሠረት፡ የሁለት ወላጆች ቢኖሩ፣ ሁለቱም ለልጆቻቸው የግብረ-ገብነት እድገት እኩል ኃላፊነት

አለባቸው። ቀዳሚ ኃላፊነታቸው ልጆቻቸውን መውድና በአኗኗራቸው ደስተኛ እንዲሆኑ መንከባከብ ነው።

መንከባከብ ሁለት ገጽታ አለው፤ እነሱም መተሳሰብ እና ለራስና ለሌሎችም ኃላፊነት መውሰድ ናቸው። ሌሎችን

ለመንከባከብ ራስን መንከባከብ አስፈላጊ መሆኑን ማስታወስ ተገቢ ነው። በተመሳሳይ እኩል ትኩረት የሚስበው

ጉዳይ ወላጆች ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ ልጆቻቸው ሌሎችን የመንከባከብ ኃላፊነት እንዲሸከሙ በመቅረጽ ነው።

ወላጆች ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ የሌሎች ጉዳይ እንዲሰማቸው፣ በሚያደርጉት ነገር ኃላፊነት መውሰድ አንዲችሉ፣

እና ማኅበራዊ ኃላፊነት መሸከም እንዲችሉ በመኮትኮት ነው።

ተንከባካቢ ወላጆች አምባገነን ያልሆኑ ባለሥልጣኖች ናቸው። በልጆቻቸው ሚዛናዊና አሳማኝ የሆነ ገደብና ደንቦች

ያስቀምጣሉ፤ ይሁን እንጂ በሚደረጉት የውሳኔ ሂደቶች ውስጥ ልጆችም በውይይቱ እንዲሳተፉ ያበረታታሉ፤

6

ተግባራዊም ያደርጋሉ። ታዛዥነት የሚመነጨው ከፍቅር እንጂ ከቅጣት ፍራቻ አይደለም። ወላጆችና በልጆች

መካከል ግልጽና በመከባባር ላይ የተመሠረተ ውይይት ይካሄዳል። ወላጆች የሥልጣናቸውን ሕጋዊነት ለማረጋገጥ

ሲሉ ውሳኔያቸውን ለልጆቻቸው ይገልጻሉ። ወላጆች የልጆቻቸውን ጥያቄና ክርክር ያዳምጣሉ፤ ሆኖም

የመጨረሻው ውሳኔ የራሳቸው ኃላፊነት መሆኑን አይዘነጉም። ወላጆች ለልጆቻቸው ተፈጥሯዊ የሆነ ፍቅርን ያሳያሉ፣

ይንከባከቧቸዋል፤ ማንኛውንም ውጫዊ ችግሮች ይመክቱላቸዋል።

የተንከባካቢ-ወላጅ ሞዴል 30 ክፍልፋዮች ሲኖሩት፣ ዝርዝራቸውና ይዘታቸው ከዚህ በታች ቀርቧል። የሞዴሉ

ክፍልፋዮች (ሀ) የግረገብነት ባህሪይ መለያዎች፣ (ለ) የልጅ-አስተዳደግ ግብረ-ገብነት፣ እና (ሐ) የሕፃን ተፈጥሮ እና

ርዕዮተ-ዓለም፣በሚባሉ ምድቦች ተፈርጀዋል። ከያንዳንዱ ክፍልፋይ ጋር በተያያዘ የተንከባካቢ-ወላጅ ሞዴልን

የሚከተሉ ሰዎች እንከን-የለሽ (ፍፁም የሆነ) የቤተሰብ ሕይዎት እንደሚገኝ የሚሰጡትን ምክኒያት በውል ለመረዳት

የሚያግዙ ገለጻዎችና ምሳሌዎች ተካተዋል።።

(ሀ) የግረገብነት ባህሪይ መለያዎች

የተንከባካቢ-ወላጅ ሞዴል፡ የግልና ማኅበራዊ ኃላፊነት፣ መንከባከብ፣ ከራስ ወገንም ሆነ ከሌሎች ጋር መተሳሰብ፣

የሌሎችን ስሜት መጋራት፣ መቻል (መታገስ)፣ መተባባር (መተጋገዝ)፣ ከፉክክርና መወዳደር ይልቅ መተጋገዝና

መተባበር፣ ራስን መቻል፤ ማኅበራዊ ትስስር፣ እና የሚቻለውን ማድረግ፣ የሚባሉ ባህሪይ መለያዎችን ያካትታል።

ይህን በተመለከተ በምሳሌዎች የታገዙ አጫጭር መግለጣዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።

(1) የግልና ማኅበራዊ ኃላፊነት፡- እራስን መንከባከብ፣ እንዲሁም ሌሎችን መንከባከብ መልካም ግብረ-ገብነት ነው።

ለራስ ኃላፊነት መውሰድ ለማኅበራዊ ኃላፊነት መሠረት ነው። (ለምሳሌ፡-“አንዳንድ ጊዜ የሌሎችን ፍላጎት ከራስህ

ፍላጎት ማስቀደም አለብህ” የሚለውን መርህ ልጆች መማር አለባቸው።)

(2) መንከባከብ፡- መንከባከብ ግብረ-ገብነት ነው። ወላጆች ልጆቻቸውን አዛኝና ርህሩህ እንዲሆኑ አድርገው ማሳደግ

አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ወላጆች ልጆቻው የሌሎች ሰዎች ፍላጎትን እንዲያጤኑ ትኩረት ሰጥተው ማስተማር

አለባቸው። ወላጆች ለልጆቻቸው የሌሎች ሰዎች ስሜት እንዲሰማቸው የሚያስችል ትምህርት መስጠት አለባቸው።

)

(3) ከራስ ወገንም ሆነ ከሌሎች ጋር መተሳሰብ፡- ከራስ ወገን ጋር መተሳሰብና መተጋገዝ መልካም ግብረ-ገብነት

ነው። በተጨማሪም ከሌሎች ወገኖች ጋር መተሳሰብና መተጋገዝ መልካም ግብረ-ገብነት ነው። (ለምሳሌ፡- ወላጆች

ልጆቻቸው ለሁሉንም ሰዎች ደህንነት እንዲያስቡና ጉዳት እንዳይደርስባቸው የሚችሉትን ሁሉ ማድረግ

እንዳለባቸው እንዲገነዘቡ ማስተማር ዋና ቁም ነገር ነው ።)

(4) የሌሎችን ስሜት መጋራት፡- ስለ ሌሎች ማሰብና መጨነቅ መልካም ግብረ-ገብነት ነው። ወላጆች ልጆቻቸው

ለሌሎች የሚያስቡና የሚጨነቁ እንዲሆኑ ማስተማር አለባቸው ። (ለምሳሌ፡- ጥሩ ወላጆች፡ ልጀቻቸው ጉዳዮችን

ሲመለከቱ፡ በራሳቸው ቦታ ብቻ ሆነው ሳይሆን በሌሎችም ቦታ መሆን እንዳለባቸው ያስተምራሉ።)

(5) መቻል (መታገስ)፡- መታገስ ግብረ-ገብነት ነው፤ መተሳሰብን ይጠይቃል። ልጆች የሌሎችን ሰዎች አመለካከት

መረዳት እና ድርጊታቸውንም መታገስ ማማር አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ልጆች የሌሎች ሰዎችን የሃዘንም ሆነዬደስታ

ስሜት መጋራት አለባቸው፤ አያገባኝም በሚል ስሜት ከሩቅ ሆነው መታዘብ የለባቸውም።)

(6) መረዳዳት፡- መረዳዳት ግብረ-ገብነት ነው። ወላጆች ልጆቻቸውን ከሌሎች ጋር ተባብረው፡ ተረዳድተውና

ተጋግዘው እንዲኖሩ ማስተማር አለባቸው፤ በተግባርም በምሳሌነት ማሳየት አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ወላጆችና ልጆች

ትብብርና መረዳዳትን ማዘውተር አለባቸው። የጋራ ዝግጅቶችንና ክንውኖችን ማዘውተር በምሳሌነት ሊጠቀስ

ይችላል።)

(7) ከመወዳደር ይልቅ መተጋገዝና መተባበር፡- ከውድድር ይልቅ መተጋገዝና መተባበር የበለጠ ጠቀሜታ አለው።

ወላጆች ልጆቻቸው ከመወዳደር ይልቅ መተባበርን እንዲያውቁና በሥራ ላይ እንዲያውሉ ማስተማርና ማበረታታት

አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ልጆች እርስ-በርሳቸው ከመፎካከር ይልቅ አብረው እንዲሠሩ መበረታታት አለባቸው።)

7

(8) ራስን መቻል፡- ፍላጎትን ማሟላትና ደስተኛ ኑሮ መኖር ግብረ-ገብት ነው። ስለሆነም ወላጆች ልጆቻቸው

ፍላጎታቸውን አሟልተው ደስተኛ ኑሮ እንዲኖሩ መርዳት አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ወላጆች ቅድሚያ ትኩረት

የሚሰጡት ነገር ልጆቻቸው ደስተኛ ስንዲሆኑና ራሳቸውን እንዲችሉ መርዳት መሆን አለበት።)

(9) ማኅበራዊ ትስስር፡- ከሌሎች ጋር ማኅበራዊ ትስስር መፍጠርና መንከባከብ ግብረ-ገብነት የተላበሰ ማህበራዊ

ባህርይ ነው። (ለምሳሌ፡- ወላጆች ስለ ልጆቻቸው የሚደሰቱበት ነገር ልጆቻው ከሁሉም ዓይነት ሰዎች ጋር ግንኙነት

ሲፈጥሩና ሲንከባከቡ ማየት መሆን አለበት።)

(10) የሚቻለውን ማድረግ፡- ልጆች በሕይዎታቸው ማስረግ የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ መበረታታት አለባቸው።

የውድድር ዓላማ መሆን ያለበት የአንድን ሰው የማድረግ ችሎታ አጉልቶ ለማውጣት እንጂ ሌሎችን ለመጉዳት

ወይም በሌሎች ላይ የበላይት ወየም የሥልጣን ጫና ለመፍጠር መሆን የለበትም ። (ለምሳሌ፡- ልጆች ውድድርን

ማየት ያለባቸው ራሳቸው የት መድረስ እንደሚችሉ እንዲማሩበት እንጂ ሌሎችን ለማሸነፍ (መጣል) እንዳልሆነ

ነው።)

(ለ) የልጅ-አስተዳደግ ግብረ-ገብነት

የተንከባካቢ-ወላጅ ሞዴል፡ የሃሳብ ልውውጥ, ኃላፊነትን መውሰድ (ተጠያቂነት)፣ በግንዛቤ ላይ የተመሠረተ

እንክብካቤ፣ ስኬታማ የመሆነ አቅምን ማሳደግ፣ የሕይዎት አማራጮችን መቃኘት (መዳሰስ)፣ በግል ላጋጠመ ችግር

መፍትሄ ማግኘት፣ ያልተቆጠበ (ያልተገደበ) ፍቅር፣ አካላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ፤ ልጆች በሚያሳዩት ግብረ-ገብነት

መኩራት፣ ጉዳት የሚያስከትል ድርጊት አለመፈፀም፣ መፀፀትና መካስ፣ ከውጫዊ ጉዳት መከላከል፣ በምሳሌነት

(በአርአያነት) መምራት፤ የመፍትሄ አማራጮች መጠቆም፤ ጣልቃ ከመግባት መቆጠብ፤ እና ከአደጉ ልጆች ጋር

መቀራረብ፤ የሚባሉ የልጅ-አስተዳደግ ግብረ-ገብነት መገለጫዎች ያካትታል። ይህን በተመለከተ በምሳሌዎች

የታገዙ አጫጭር መግለጣዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።

(11) እርስ በርስ መከባበር፡- በወላጆችና በወላጆች መካከል ያለው መከባበር የጋራ መሆን አለበት። ወላጆች

በልጆቻቸው የሚከበሩትን ያህል፣ ልጆችም በወላጆቻቸው መከበር አለባቸው። (ለምሳሌ፡- በልጆችና በወላጆች

መካከል መከባበር መኖር አለበት።)

(12) የሃሳብ ልውውጥ፡- የልጆችና የወላጆች የእርስ በርስ የሃሳብ ልውውጥ “ወሬ በዐይን ይገባል” በሚባለው ደረጃ

የሚደርስ መቀራረብ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። ልጆች በቁም-ነገር መደመጥ አለባቸው። ልጆች በወላጆችን

ውሳኔዎች ላይ ጥያቄ እንዲያነሱ ከተበረታቱ፣ የወላጆቻቸውን ምክኒያታዊነት ሊረዱ ይችላሉ፤ ብሎም ከሂደቱ

ትምህርት ያገኙበታል። (ለምሳሌ፡- ልጆችና ወላጆች ሃሳባቸውን በግልጽ መለዋወጥ ጠቃሚ ሂደት መሆኑ ግንዛቤ

ማግኘት አለበት።)

(13) ኃላፊነትን መውሰድ (ተጠያቂነት)፡- ወላጆች በልጆቻቸው ተጠያቂነት አለባቸው፤ በመሆኑም ወላጆች ስለ

ውሳኔዎቻቸው ለልጆች በግልጽ ማሳወቅ ካስፈለገም በቂ ማብራሪያ መስጠት አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ወላጆች

ልጆቻቸውን በተመለከተ በሚወስኗቸው ውሳኔዎች ግልጽነት ማሳየት አለባቸው።)

(14) በግንዛቤ ላይ የተመሠረተ እንክብካቤ፡- በእውነት ለመንከባከብ ከተፈለገ ወላጆች የልጆቻቸውን ሁኔታ በውል

ማጤን አለባቸው፤ የልጆቻቸውን ችግር በልጆችም ቦታ ሆኖ መመዘን ይኖርባቸዋል፤ እንክብካቤ ሁሉ የተሟላ

ፍቅር መልበስ አለበት። (ለምሳሌ፡- ወላጆች ለልጆቻቸው ተጨባጭ እንክብካቤ ለማድረግ ከተፈለጉ ልጆቻቸው

ያሉበትን ሁኔታ በቀርበት መከታተል አለባቸው።)

(15) ስኬታማ የመሆነ አቅምን ማሳደግ፡- ወላጆች ልጆቻቸው ዓላማቸውን ከግብ በማድረስ ስኬታማ ውጤት

እንዲያገኙ የሚያስችል ግብረ-ገብነት እንዲላበሱ ጥረት የማድረግ ግዴታ አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ወላጆች በተቻለ

መጠን ልጆች ህልማቸውን ከግቡ ለማድረስ የሚስችል አቅም እንዲኖራቸው መጣር አለባቸው።)

(16) የሕይዎት አማራጮችን መቃኘት (መዳሰስ)፡- ወላጆች፡ ልጆቻቸው የሕይዎት አማራጭ መንገዶችን እንዲቃኙ

(እንዲዳስሱ) አመቺ ሄነተራ መፍጠር አለባቸው። (ለምሳሌ፡- በሕይዎት ውስት ያሉ አማራጮች ቁጥር-ስፍር

የላቸውም። ልጆች ሊከተሉት የሚገባ፡ ፍቱን የሆነ አንድ ዓይነት መንገድ የሚባል የለም።)

8

(17) በግል ላጋጠመ ችግር መፍትሄ ማግኘት፡- ፍትሃዊ ማለት እያንዳንዱ ልጅ በግል ያለበትን (ያለባትን) ችግር

ለማቃለል የሚያስችል መፍትሄ ማግኘት ማለት ነው። (ለምሳሌ፡- ለማንኛውም ልጅ ከወላጅ የሚሰጥ ድጋፍ ልጁ

(ልጅቱ) በግል ካጋጠመው (ካጋጠማት) ችግር ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት።)

(18) ያልተቆጠበ (ያልተገደበ) ፍቅር፡- ወላጆቻቸው ለልጆቻቸው ያልተቆጠበ (ያልተገደበ) ፍቅር መስጠት

አለባቸው። ከወላጆች ለልጆች የሚሰጥ ፍቅር፡ በልጆች መታመም ወይም ጤና መሆን፡ ማጥፋት ወይም ማልማት፡

አካል መጉደል ወይም አለመጉደል፡ ወይም ሌላ ሁኔታ ጋር ጋር እተዛመደ የሚሰጥ ወይም የሚነፈግ ሳይሆን ልጆች

በመሆናቸው ብቻ ማግኘት ማግኘት አለባቸው። (ለምሳሌ፡- ምንም ይሁን ምን ልጅ የወላጆችን ፍቅር ማግኘት

አለበት።)

(19) አካላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ፡- ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በአካልም ይሁን በመንፈስ መቀራረብ አለባቸው።

(ለምሳሌ፡- ወላጆች ከልጆቻው ጋር የአካልና የመንፈስ መቀራረብ መፍጠር አለባቸው።)

(20) ልጆች በሚያሳዩት ግብረ-ገብነት መኩራት፡- ወላጆች ልጆቻቸው በድርጊታቸው ሁሉ ግብረ-ገብነትን

እንዲከተሉ ማነሳሳት አለባቸው። ወላጆች ልጆቻቸው ግብረ-ገብነት ባለው መልኩ ተግባራቸውን ሲያገናውኑ

ልኮሩባቸው ይገባል። ወላጆች ልጆቻቸውን ቀና መንገድ እንከተሉ ሳይታክቱ በምክርም በምሳሌነትም ዘዴ

ተጠቅመው ሊያስተምሯቸው ይገባል። (ለምሳሌ፡- ወላጎች ሌጆቻው በሌሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ መምከር፤

ካደረሱም ድርጊታቸው ነውር መሆኑንና እነሱንም ድርጊቱ እንዳሳዘናቸው ለልጆቻው መንገር።) ወላጆች

ለልጆቻቸው የግብረ-ገብነት ባህርይ የሚያኮራና የሚያስከብር ብሎም ደስታን የሚያስገኝ መሆኑን ማስተማር

አለባቸው። ልጆች የግብረ-ገብነት ባህርይ የሚቀበሉት የቁሳቁስ ሽልማት ስለሚያስገኝ ወይም አካላዊ ቅጣት ጋር

ስለሚያስከትል መሆን የለበትም። (ለምሳሌ፡- ልጆች ወላጆቻቸው በእነሱ እንደሚኮሩ ካረጋገጡ ስኬታማ ለመሆን

የሚቻላቸውን ሁሉ ከማድረግ አይቆጠቡም።)

(21) ጉዳት የሚያስከትል ድርጊት አለመፈፀም፡- ወላጆች በልጆቻቸው የአካላዊ ጉዳት ወይም አእምሯዊ ጉዳት

ፈጽሞ ማድረስ የለባቸውም። (ለምሳሌ፡- ወላጆቻው ልጆቻቸውን ለመቅጣት መግረፍን፡ መቆንጠጥን፡ ጥፊን፡

መስደብን፡ ወዘተ፡ እንደ አማራጭ መጠቀም በልጆች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል መረዳት አለባቸው።)

(22) ከውጫዊ ጉዳት መከላከል፡- ወላጆች ልጆቻቸውን ከውጫዊ ጉዳት መጠበቅ (መከላከል) አለባቸው።

(ለምሳሌ፡- ወላጆች ልጆቻቸውን ወድቀው ወይም ተንከባለው ግጭት ከሚፈጥሩ ቁሳቁሶች፡ ከሚቆርጡ ስለቶች፡

መርዛማ ነገሮች፡ ወዘተ. መጠበቅ አለባቸው።)

(23) ጥፋትን ማወቅ፡ መፀፀትና ይቅርታ መጠየቅ፡- ጥፋትን ማወቅ፡ መፀፀትና ማረም፤ ለወደፊትም ተመሳሳይ ነገር

እንዳይፈጠር ጥንቃቄ ማድረግ መልካም ግብረ-ገብነት ነው። (ለምሳሌ፡- ልጆች በሌሎች ላይ ጥፋት ቢሠሩ፤

ጥፋታቸውን ተረድተው በመልካም ምግባር መካስ አለባቸው ወላጆቻቸው ሊመክሯቸው ይገባል።)

(24) በምሳሌነት (በአርአያነት) መምራት፡- ወላጆች ልጆቻቸውን በምሳሌነት (በአርአያነት) መምራት አለባቸው።

ወላጆች ልጆቻቸው እንሲሠሩት የሚፈልጉትን ነገር ራሳቸው ሠርተው ማሳየት አለባቸው። ወይም ልጆቻቸው

እንዳይሠሩት የሚፈልጉትን ነገር ራሳቸውም ለልጆች በተጋለጠ ሁኔታ ከመሥራት መቆጠብ አለባቸው። (ለምሳሌ፡

- ልጆች ወላጆች የሚናገሩትን ያዳምጣሉ፡ የሚሠሩትን ያያሉ፡ ከዚያ በኋላ እነሱም ወላጆቻቸውን በመምሰል

(በመኮረጅ) ወላጆቻቸው የተናገሩትን ለመናገር፡ ያደረጉትን ለማድረግ ይሞክራሉ።)

(25) የመፍትሄ አማራጮች መጠቆም፡- ልጆች በአንድ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ሲሰጡ ወላጆች የመፍትሄ አማራጮች

በመጠቆም በኩል ሊረዷቸው ይችላሉ። ይሁን እንጂ ወላጆች ራሳቸው ለብቻቸው ወስነው ውሳኔያቸውን ልጆች

እንዲቀበሉት ማስገደድ የለባቸውም። (ለምሳሌ፡- “ለራስህ የሚበጅህን ራስህ አሰላስለህ፡ አውጥተህና አውርደህ

መለየት አለብህ” የሚለውን ማበረታቻ ነው ወላጆች አዘውትረው ለልጆቻቸው መንገር ያለባቸው።)

(26) የተመጠነ ጣልቃ-ገብነት፡- ወላጆች በልጆቻቸው ባህርይና ምርጫ ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠር የለባቸውም፤

ጣልቃ-ገብነታቸው የተመጠነ መሆን አለበት ። (ለምሳሌ፡- ወላጆች ልጆቻቸው ራሳቸውን እንዲሆኑ ሊፈቅዱላቸው

ይገባል።)

9

(27) ከአደጉ ልጆች ጋር መቀራረብ፡- ወላጆችና የአገደጉ-ልጆች እንደ ጓደኛ መቀራረብ፡ መረጃ መለዋወጥ፡ እና

መወያየት አለባቸው። (ለምሳሌ፡- የአደጉ ልጆች ወላጆቻቸውን ምክርና እርዳታ የመጠየው ምቾች ሊኖራቸው

ይገባል።)

(ሐ) የሕፃን ተፈጥሮ እና ርዕዮተ-ዓለም

በተንከባካቢ-ወላጅ ሞዴል ይዘት ውስጥ የተካተቱት የግረገብነት ባህሪይ መለያዎች፣ የልጅ-አስተዳደግ ግብረ-ገብነት

ከየሕፃን ተፈጥሮ እና ዓለማዊ እምነት ጋር በጥብቅ የተሳሰሩ ናቸው። ልጆች ጥሩ ሆነው ነው የሚወለዱት፣ የድርጊት

ውጤት ከብዙ ነገሮች ጋር የተያያዘ ነው፣ የሴቶችና የወንዶች እኩልነት፣ የሚባሉ የሕፃን ተፈጥሮ እና ዓለማዊ

እምነት መገለጫዎች ያካትታል። ይህን በተመለከተ በምሳሌዎች የታገዙ አጫጭር መግለጣዎች እንደሚከተለው

ቀርበዋል።

(28) ልጆች ጥሩ ሆነው ነው የሚወለዱት፡- ልጆች ጥሩ ሆነው ነው የሚወለዱት፡ የሚፈልጉትም ጥሩ ነገር መሥራት

ነው። ልጆች ከሌሎች ጋር ለመረዳዳት፡ ለመተባበር፡ እና ለመተሳሰብ ተፈጥሯዊ ዝንባሌ አላቸው (ለምሳሌ፡-

ወላጆች ልጆቻቸው የሚያሳዩትን ተፈጥሯዊ የሆነ ጥሩ ባህርይ ማበረታታት አለባቸው።)

(29) የድርጊት ውጤት ከብዙ ነገሮች ጋር የተያያዘ ነው፡- በዓለም ላይ አስካሁን፡ አሁን፡ እና ወደፊት የነበሩ፡ ያሉ፡

እና የሚመጡ፡ በግለሰብ ላይ የሚደርሱ አብዛኞቹ ከስተቶች ከግለሰብ ቁጥጥር ውች ናቸው። (ለምሳሌ፡- በልጆች

ሕይወት ላይ የሚደርሱ መጥፎ-አጋጣሚዎች የሚፈጥሩበት ምክኒያት ውስብስብ ነው፤ ጥቂቶቹ በልጆች ስህተት

ሊሆን ቢችልም አብዛኛዎቹ ግን ከልጆች ቁትጥር ውች ናቸው።)

(30) የሴቶችና የወንዶች እኩልነት፡- ሴቶችና ወንዶች እኩል ባለ መብቶች ናቸው፤ ኃፊነታቸውና ሥልጣናቸውም

እኩል ነው። (ለምሳሌ፡- የወላጅነትን ኃላፊነት ለመከፋፈል ሴት ወይም ወንድ መሆን ዋና መሥፈርት አይደለም።)

4.4 ተራማጅ ፖለቲካዊ ራዕይ

የተንከባካቢ ወላጅ ሞዴልን ለፖለቲካው ብናውለው የምናገኘው የተራማጅ ግብረ-ገብነትንና ፖለቲካዊ ፍልስፍና

ነው። በዝርዝር ሲታይ የተራማጅ አስተሳሰብ ውስብስብ ነው። ይሁን እንጂ ከፍተኛዎቹ የግብረ-ገብነት እሴቶችና

አጠቃይ መርሆች ቀላልና ቀጥተኛ ናቸው።

ልክ እንደ ተንከባካቢ ወላጆች ሞዴል፡ የተራማጅ ግብረ-ገብነት በመተሳሰብ እና በኃላፊነት ላይ የተመሠረተ ነው።

መተሳሰብ (Empathy)፡- ሌሎች ምን እንደሚሰማቸው መረዳት፣ ራስን በሌለው ቦታ አድርጎ ማየት፣ እና ስለ ሌሎች

ማሳብ፡ መጨነቅና መሥጋት፣ የሌሎችን የደስታና የሃዘን ስሜት መጋራት፤ ከሌሎች ጋር ከፉውንም ሆነ ደጉን

መጋጋት፤ መቀራረብና በሄተሰብነት መልክ መተያየትን ያካትታል።

ኃላፊነት (Responsibility)፡- መተሳሰብንና ኃላፊነትን ለራስም ሆነ ለሌሎች ጥቅም እንዲውል ማድረግ ማለት

ነው።

ከመተሳሰብና ከኃላፊነት የሚመነጩ አንኳር የተራማጅ እሴቶች አሉ። እነዚህ እሴቶች በማንኛው ጉዳይ ላይ

የተራማጅ አስተሳሰብና ቅርፅ፣ እንዲሁም የተራማጅ አቋም ምን ሊሆኑ አንደሚችሉ ይጠቁማሉ። ተራማጅ የፖለቲካ

ሞዴልን ሥራ ላይ ለማዋል መሠረት የሚሆኑ ከመተሳሰብ የሚመነጩ እሴቶች ክምችት የሚከተሉትን ያካትታል።

 መከላከል (Protection) (ችግርና አደጋ ለተጋረጠባቸው ወገኖች)

 ስኬት (አንተ እንደምትፈልገው ሁሉ ሌሎችም ትርጉም ያለው ኑሮ እንዲኖሩ)

 ነፃነት (ስኬታማ ለመሆን ነፃ መሆን ያስፈልጋል፤)

 መልካም አጋጣሚ (Opportunity) (ምክኒያቱም ስኬታማ ለመሆን ትርጉም ያለውና ፍሬያማ ውጤት

ለማግኜት የሚያስችሉ አጋጣሚዎችን መዳሰስ ስለሚያስፈልግ)

 ሚዛናዊነት (Fairness) (ምኒያቱም አድሏዊ ሁኔታ ነፃነትንና አጋጣሚን ስለሚያሳጣ)

10

 እኩልነት (Equality) (ምክኒያቱም መተሳሰብ ለሁሉም ስለሚዳረስ)

 ሀብት (Prosperity) (ምክኒያቱም ወደ ስኬት ለማምራት መነሻ የቁሳቁስና የገንዘብ፤ እንዲሁም በቂ

መጠለያ፡ ምግብ፡ እና ጤና ያስፈልጋል፤)

 ማኅበረሰብ (Community) (ምክኒያቱም ማንም ሰው ብቻውን መሆን ስለማችል፣ ለማኝናውም ሰው

ስኬታማ ኑሮ ለመኖር ማኅበረሰቦች አስፈላጊ ናቸው፤)

ሌሎችን ለማገዝ መጀመሪያ ራስህን መቻል እንዳለብህ ማስታወስ አለብህ። በተራማጅ ግብረ-ገብነት ራስህን

መንከባከብና ሌሎችን መንከባከብ አይቃረኑም፤ ምክኒያቱም ራስህን ካልተንከባከብህ ሌሎችን ለመንከባከብ

አትችልም።

እንዚህን የተራማጅ አሴቶች የሚያቅፉ አራ ቁልፍ ፖለቲካዊ መርሆች አሉ። እነዚህ መርሆች ተራማጆች

በሚያርቧቸው ውይይቶች፡ ክርክሮች፡ ፖሊሲዎችና ፕሮግሞች ተደጋግመው ይነሳሉ።

(1) የጋራ ደህንነት መርህ

በግላዊ ፍላጎትና ምኞታችን ግለሰባዊ ነን። ግን እንደ ሀገር በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ መሻሻልን ከፈለግን፣ እንደ

ሕዝብ ሁላችንም አንድ ላይ ወደላይ እንወጣለን ወይም ሁላችንም አንድ ላይ ወደታች አንወርዳለን። በአጭሩ

ለግለሰባዊ ደህንነታችን የጋራ ደህንነት አስፈላጊ ነው። ዜጎች ተባብረው የጋራ ሀብት በመፍጠር ለጋራ ደህንነት

ማዋል የጋራ ጥውም ያስገኛል። ውሃ፡ መንገድ፡ ትምህር ቤት፡ ክሊኒክ፡ ወዘተ. ቢሠራ ሁሉም በጋራ ተጠቃሚ

ከመሆኑም በላይ፣ ሰዎች ግለሰባዊ ፍላጎትና ምኞታቸውም እንዲሳካለቸው ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል።

እዚህ ላይ የታክስ ካፋዮች ገንዘብ (የጋራ ሀብት) ለምን ለምን እንደሚል ማየት ተገቢ ነው። የጋራ ሀብት ለሀገር

መገናኛ የሚሆን የመንገድ መረብ፣ ለደህንነት ሥርዓት (ፖሊስና ወታደር)፤ የባንክ ሥርዓት፣ የፍር ቤት ሥርዓት፣

እና ሌሎች ይውላል። በታክስ መልክ የተሰበሰበው የጋራ ሀብት፡- ብድር (የባንክ ሥርዓት)፣ ውሎችን ማስከበር

(የፍርድ ቤት ሥርዓት)፣ የመገናኛ ሥርዓት (ኢነተርኔትና የሳተላይት ሥርዓት)፣ እቃን ማጓጓዝ (የመንገድ ሥርዓት)፣

ለመሳሰሉት የሀብት ማመንጫ እንቅስቃሴዎች ይውላል።

ይህም በበኩሉ የኑሮ ስኬትን ለሚፈጥሩ ሁኔታዎች አጋጣሚዎችን ስለሚፈጥር የጋራ ደህንነትን ያጠናክራል። አንድ

ሰው ብዙ ገንዘብ ሲያገኝ በጋራ ሀብት የበለጠ ተጠቃሚ ይሆናል። ይህ ሁኔታ እንደገና የጋራ ሀብት ሥርጭት

እንዲሠፋ፡ አንዲዳብር፡ እንዲጠበቅና ደረጃው አንዲሻሻል የበለጠ ኃላፊነት ያስከትላል። በዚህ አመለካከት ነው

ታክስን በተመለከተ የተራማጅ ግብረ-ገብነት የመሠረተው።

የጋራ ሀብት ለጋራ ደህነት ነፃነት ይፈጥራል። ከፍርሃትና ከሰቆቃ ነፃ በመሆን የደህነት ዋስትና የሚረጋገጠው የጋራ

ሀብት አጠቃቀም ለሁሉም ዜጎች በሚበጅ መልክ አገልግሎት ላይ ሲውል ነው።

የጋራ ደህንነት መርህ ፍትሃዊነትንና እኩልነትን ያራምዳል። ተራማድ መንግሥት አድሏዊ አሠራርን ይከላከላል፤

የአቅመ-ቢሶችን ፍላጎትና ምኞች በመጠበቅ ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይንቀሳቀሳል። ተራማጅ መንግሥት የሚመራው

“የአስመ-ቢሶች ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነው፤ ብቻቸውን አይደሉም”፤ በሚለው መርህ መሠት ነው። ይህ ማለት

ሁላችንም ከጥቅሙ መጋራት ብቻ ሳይሆን ኃላፊነቱንም መጋራት አለብን ማለት ነው።

የጋራ ሀብትን ለጋራ ደህንነት መጠቀም ተጨማሪ ሀብት ይፈጥራል፣ ይህ ደግሞ በበኩሉ ለኅብተሰቡ ኑሮ መሻሻል

ይበጃል። የጋራ ደህነት መርህ ግብረ-ገብነት ያለው የሀብት ማፍራትን አሠራር ይፈጥራል። ግብረ-ገብነት ያለው

የሀብት ማፍራትን አሠራር በግለሰቦች፣ በማኅበረሰቦች፣ ወይም በተፈጥሮ ላይ ጉዳት አያደርስም። ለሕዝብ፡

እንዲሁም ለቅር ሠራተኞችና ለማኅበረሰቡ ተጨባጭ ጥቅም ያስገኛል። ጠራማጅ መንግሥት ግብረ-ገብነት

ያላቸውን ሀብት አፍሪዎች ያበረታታል፤ ይደግፋል። በሌላ በኩል ደግሞ ግብረ-ገብነት በጎደለው መንገድ ሀብት

የሚያፈሩትን ደግሞ ከአስነዋሪ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል።

የጋራ ደህንነት መርህ ማለት ቀደም ብሎ ከተጠቀሱት በተጫማሪ የጋራ የሆኑ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ንብረትን፣

ታሪካወ ቅርሶችን፣ ባህላዊ እሴቶችን፣ እና የመሳሰሉትን መጠበቅን ያካትታል።

(2) የነፃነት መርህ መስፋፋት

11

ተራማጅ ሞዴል ግብረ-ገብነት እሴቶች የመሠረታዊ ነፃነቶች በውል እንዲታወቁና እንዲከበሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ

አድርገዋል። የመምረጥና የመመረጥ መብቶች፣ የሰራተኞች መብቶች፣ ሁሉን-አቀፍ የትምህርትና የጤና አገልግሎት፣

የሸማቾች ጥበቃ፣ ሲቪል መብቶች፣ የመሳሰሉትን በማክበርና በማስከበር ረገድ የሚያስመሰግን ውጤት

አስመዝግበዋል።

(3) የሰብአዊ ክብር መርህ

መተሳሰብ ለመሠረታዊ የሰብአዊ ክብር እውቅና መስጠትን እና እውን እንዲሆንም ኃላፊነት ወስዶ ተግባራዊ

ማድረግን ይጠይቃል።

የሰብአዊ ክብር መርህ ለበርካታ የተራማጅ አቋሞች መሠረት ነው። የማሰቃየት ምርመራ ለመቃወምን፣ የዘር-

ማጥፋትን ወንጀል ለመከላከልን፣ ለድሆች መሠረታዊ ፍላጎቶች እንዲሟሉ ጥረት ማድረግን፣ የሴቶ የእኩልነት

መብት እንዲጠበቅ መታገልን፣ ዘረኝነትን ተቃውሞ ትግል መደገፍን፣ ወዘተ. የመሳሰሉት መሠረታቸው የሰብአዊ

ክብር መርህ ነው።

እንደ ሀገር የሰብአዊ ክብር ድንበር የት እንደሚደርስ መወሰን አለብን። ምግብ፡ መጠለያ፡ ትምህርት‹ የጤና

እንክብካቤ ለሁሉም ዜጎች መሠረታዊ መብቶች መሆናቸው እውቅና ማግኜት አለበት። የተራማጅ የሰብአዊ ክብር

መርህ መሠረት እነዚህ መብቶች ላይ ትኩረት በመስጠት ለሁሉም ዜጎች ደህንነት ዋስትና መስጠት ይቻላል።

(4) ብዝህነት (Diversity) መርህ

መተሳሰብ በማኅበረሰቦች ውስጥ ጤነኛ-ግኑኝነት መጠናከርን ያመለክታል። ይህ ደግሞ በማኅበረሰቦች፣ በትምህር

ቤቶች፣ እና በሥራ ቦታዎች አንድነት-በልዩነት ሁኔታ መስፈኑን ያሳያል። አንድነት-በልዩነት መርህ ለዜጎች ሁሉ

ትርጉም ያለው አመቺ ሁኔታ እንዲፈጠር ያስችላል።

“ብዝህነት” በዘር፡ በጎሣ፡ በሃይማኖት፡ በፆታ፡ በሃብት፡ በትምህርት፡ ወይም በሌሎች ልዩነቶች ሰበብ የሚከሰት

የአድሎን ለመታገል የሚያግዝ የተራማጅ መርህ ነው።

“ብዝህነት” የሚለውን በገባያ መልክ ማየት ይቻላል። ለምሳሌ፡- አንድ አይነት ሰብል በአንድ ቦታ ትርፍ ምርት፣

በሌላ ቦታ የምርት እጥረት፣ በሌላ ቦታ ደግሞ ምንጊዜም ቢጎን የማይመረት ሊሆን ይችላል። እነዚህን በሦስቱ

ቦታዎች ያሉ ሰዎች በፍላጎታቸው ይለያያሉ፣ ሁሉም ብቻቸውን ፍላጎታቻውን ለማሳካት አይችሉም። ስለሆነም

የምርቱን ሥርጭት ለማስተካከል ከተፈለገ ሁሉም ገበያ መውጣት አለባቸው። የተለያዬ ችግራቸውን እንደያዙ ገባያ

ውስጥ ቢገናኙ የሦስቱንም ችግር ሦሰቱ በጋራ ሊፈቱት ይችላሉ። በገበያ አማካይነት ትርፍ ያለው ይሸጣል፤

የጎደለበት ሸምቶ ያስተካክላል፤ ምንም የሌለው የሚያስፈልገውን ያህል ይሸምታል፤ አንድ ቦታበመገናኘታቸው

የሁሉም ችግር መፍትሄ አገኘ ማለት ነው።

4.5 የወግ አጥባቂ ፖለቲካዊ ራዕይ

የወግ-አጥባቂ ግብረ-ገብነት ማዕከል የሚያደርገው በሥልጣንና ቁጥጥር ጉዳዮች ላይ፤ ማለትም ራስን-በመቆጣጠር

(ዲሲፕሊን) እና ሌሎችን በመቆጣጠር ጉዳይ ላይ ነው።

ሥልጣን ሕጋዊና ግብረ-ገብነት የተላበሰ መሆን አለበት። ባለሥልጣኖች ኃይል አላቸው፤ መልካም ግብረ-ገብነት

ስላላቸውም ሌሎችን የመቆጣጠር ሕጋዊነትን ያላብሳቸዋል። የፖለቲካ ባለሥልጣን የተመረጠ እና ብሎም ሕጋዊ

የግብረ-ገብነት ሥልጣን ስላለው መከበር አለበት።

ከዚህ ከባለሥልጣንነትና ከተቆጣጣሪነት ጋር የሚያያዙና የሚከተሉ ሌሎች እሴቶች አሉ።

ሥን-ሥርዓት፡- ራስን መቆጣጠር ወሳኝ ችሎታ ነው። ግብረ-ገብነት ጋር የተቆራኘ ሥልጣን አንድ ሰው ሲያጠፋ

በሚደርስበት ቅጣት አማካይነት የሚማረው ውስጣዊ ሥን-ሥርዓት ነው። የባለሥልጣን አጥፊን ያለመቅጣት

ውድቀት የግረ-ገብነት ውድቀት ነው ተብሎ ይታመናል።

12

ይህ ዓይነት አመለካከት የሚያስከትላቸው ፖለቲካዊ ቀውሶች አሉ። አንድ ሰው በራሱ ያላፈራውን ማግኘት ግብረ-

ገብነት የጎደለው ድርጊት ነው። ሀብት የሌለው ሰው በቂ ሥነ-ሥርዓት ስለሌለው ነውና ድሃ መሆኑ የሚገባው ነው።

ለሌላቸው ሰዎች እገዛ የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ሥነ-ሥርዓት እንዲዳከም የሚያደርጉ በመሆናቸው ግብረ-

ገብነትን ጥሰዋል ተብለው ይኮነናሉ።

ባለቤትነት (Ownership): አንድ ሰው በገባያ አማካይነት ወይም በሕጋዊ መንግድ ያገኘውን ንብረት እንደፈለገው

የማድረግ መብት አለው። ማንም ሰው ገንዘቡን ከመንግሥት አተቃቀም በተሻለ መንገድ የመጠቀም ችሎታ አለው።

የጋራ ሀብት ለጋራ ደህንነት መዋል ያለበት ለአካላዊ ደህነት ጥበቃ ብቻ ሲውል ነው። ትርፍ ማግኘት ከሁሉም

በላይ ተፈላጊ ነው። ለትርፍ ተነሳሽ ያልሆነ መንግሥት ብቃት የሌለው አባካኝ ነው። እንደዚህ አይነት መንግሥት

በሚፈጥራቸው የቁጥጥር ደንቦች፡ ታክስ ጫማሬ፡ ማኅበራትን ማጠናከር፤ ክስ ምስረታ ምክኒያት በገባያ ሥርዓት

ላይ እንቅፋት ይጋረጣል።

የሥልጣን ተዋረድ (Hierarchy): ኢኮኖሚያዊ፡ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተዋረድ ተፈጥሯዊ ነው፤ ምክኒያቱም

የተወሰኑ ሰዎች ከሌሎች የበለጠ ችሎታና ሥነ-ሥርዓት ስላላቸው ነው። ሰለሆነም ከሌሎች የበለጠ ማግኘት

ይገባቸዋል ተብሎ ይታመናል።

የወግ-አጥባቂነት ፍልስፍና ለተራጅነት መርህ እውቅና አይሰጥም። ለምሳሌ፡- “የጋራ ደህንነት መርህ” ለሥነ-ሥርዓት

ዋጋ በሚሰጠው በነፃ-ገበያ ሥርዓት ላይ ጣልቃ ይገባል።

በተራማጆች እንዲሠፋ የሚፈልጉት ነፃነት፣ በተለይም - ከሰቆቃና ከሥጋት ነፃ መሆን - የሚለው አስተሳሰብ በወግ-

አጥባቂዎች ዘንድ ተቀባይነት የለውም።

“የሰብአዊ ክብር መርህ”ም በአብዛኛዎቹ ወግ-አጥባዊዎች ዘንድ ተቀባይነት የለውም። ምክኒያቱም ሰዎች ተፈጥሯዊ

ክብር የላቸውም፤ ሰዎች ክብራቸውን ማረጋገጥ የሚችሉት ባላቸው ሥነ-ሥርዓት ነው። ሰዎች ክብር ያላቸው

መሆኑን ማረጋገጥ ያለባቸው በሥራቸው ብቻ ነው። አንዳንድ ለየት ያለ አመለካከት ያላቸውም አሉ። ፈሪሃ-

እግዚአብሔር ያላቸውና ወግ-አጥባቂነት እምነት ያላቸው ጠንካራ ሠራተኞች የሆኑ ሰዎች የግለሰብ ችሮታ

(ምጽዋት) ሊያገኙ ይገባቸዋል የሚሉ አሉ። ይሁን እንጂ በመሠረታዊ የወግ-አጥባዊዎች እምነት መሠረት ሰዎች

ሰብአዊ ፍጡር በመሆናቸው ብቻ ክብር ይገባቸዋል አይባልም።

ከተራማጆች መርህ አንጻር ደግሞ ወግ-አጣባቂዎች የሚከተሉት መርሆች አሏቸው።

የግብረ-ገብነት መርህ፡- ግብረ-ገብነት የሚመጣው ሕጋዊ የግብተ-ገብነት ባለሥልጣኖችን በመታዘዝ ነው። ለዜጎች

የመንግሠት ሕግ፡ ለልጆች ወላጆች፡ ለተማሪዎች አስተማሪዎች፡ ለስፖርተኞች አሠልጣኞች፡ ለወታደሮች አዛዦች፡

ወዘተ. የግበረ-ገብነት ባለሥልጣኖች ናቸው።

የግለሰብ ኃላፊነት መርህ፡- ሁሉም ሰው በግል የራሱን እጣ ፈንታ የመወሰን ኃላፊነት አለበት። ቢሰካለት፣

ስለሚገባው ነው። ባይሳካለት ደግሞ የራሱ ጥፋት ነው። ማንኛው ሰው የራሱን ጉዳይ የሚወስው ራሱ ከሆነ

የሥራው ውጤት ጥሩም ይሁን መጥፎ ባለሄቱ እራሱ ነው።