የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎች በአማራ ክልል 2007

የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎች በአማራ ክልል 2007

የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎች በደቡብ ክልል 2007

የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎች በደቡብ ክልል 2007

የሰማያዊ ፓርቲ ተወዳዳሪዎች በኦሮሚያ ክልል 2007

የሰማያዊ ፓርቲ ተወዳዳሪዎች በኦሮሚያ ክልል 2007

ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ቦርድ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠየቀ

• ‹‹በሰማያዊ እና በፀጥታ ኃይሎች መካከል ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂው የከተማ አስተዳደሩ ነው››
ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት ሚያዝያ 29/2007 ዓ.ም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በላከው ደብዳቤ ምርጫ ቦርድ በህግ የተሰጠውን ኃላፊነት እንዲወጣ ጠይቋል፡፡ የተሻሻለውን የምርጫ ህግ 532/1999 ዓ.ም አንቀፅ 58 ቁጥር 1 ላይ ‹‹አንድ ዕጩ ተወዳዳሪ መታወቂያ ካገኘበት ቀን አንስቶ ምርጫው ሁለት ቀን እስኪቀረው ድረስ ከአስተዳደሩ ሆነ ከማዘጋጃ ቤት ፈቃድ ሳይጠይቅ በፅሁፍ በማሳወቅ ብቻ የድጋፍ ስብሰባዎች አሊያም ሰላማዊ ሰልፎችን የመጥራት መብት አለው›› የሚለውን የጠቀሰው ሰማያዊ ፓርቲ ሆኖም ይህንን መብት መነፈጉን ገልጾአል፡፡

በአዲስ አባባ የሰማያዊ ፓርቲ የተወካዮች ምክር ቤት ተወዳዳሪዎች

ሰማያዊ በከተማው ካስመዘገባቸው 23 እጩዎች ውስጥ ሊቀመንበሩን እና ሁለት ሴቶችን ጨምሮ አራት እጩዎች በእጣ ከተወዳዳሪነት ውጪ ሲሆኑ የተቀሩት ሁለት እጩዎች ደግሞ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት የተወዳዳሪነት መብታቻው ተገፏል!

የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ 2007 ዓ/ም ማኒፌስቶ


ይህ የምርጫ ማኒፌስቶም ሀገሪቱ አሁን ካለችበት የኢህአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሚደረግ ሽግግር ወቅት በሀገራችን ሰማያዊ ፓርቲ በምርጫ ተወዳድሮ ማሸነፍ ቢችል የሚያከናውናቸውን ተግባራት በዝርዝር የሚተነትን ነው፡፡ ይህ የምርጫ ማኒፌስቶ በዋናነት በሦስት ምዕራፍ የተከፈለ ሲሆን የመጀመሪያው የፖለቲካ ሥርዓቱ አደረጃጀት ምን መምሰል እንዳለበት የሚገልፅ ክፍል ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ሰማየዊ ፓርቲ ባለፉት 24 ዓመታት የህወሀት/ኢህአዴግ መራሹ ሥርዓት በሀገራችን ላይ የፈፀማቸውን የተሣሣቱ የፖለቲካ ሂደቶች በዝርዝር የሚያስቃኝ ሲሆን፤ በአንፃሩም ፓርቲው በሥልጣን ላይ ቢቀመጥ በዋነኛነት በቋንቋ ላይ የተመሰረተውን የፌደራል ሥርዓት በመቀየር መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥን፣ የሕዝብ አሰፋፈርንና፣ ልማትና ሌሎች ማህበራዊ ትስስሮችን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ለማድረግ እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡ በመንግሥት አወቃቀሩ፣ በነፃ-ፕሬስ፣ በመከላከያ ፖሊስና ደህንነቱ አወቃቀር እንዲሁም የውጭ ግንኙነት አማራጭ ፓሊሲውም በዝርዝር በማኒፌስቶው ላይ የተቀመጡ አንኳር ጉዳዮች ናቸው፡፡ .....

የሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ቅስቀሳ መግለጫ

ሰማያዊ ፓርቲ ሲቋቋም በኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓት ለውጥ ለማምጣት በሚያደርገው ትግል በሁሉም ዘርፎች ግልፅ እና ዝርዝር የሆኑ አማራጭ የፖሊሲ ሃሳቦችን ያዘጋጀ ቢሆንም በያዝነው ዓመት ለሚካሄደው ምርጫ በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምርጫ ቅስቀሳ መግለጫ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ እንደሚታወቀው አሁን ሀገሪቱ የምትመራበት ሕገመንግስት በየአምስት ዓመቱ በሚካሄድ አጠቃላይ ምርጫ መንግስት እንዲመሠረት የሚፈቅድ በመሆኑ እና ይህም በትክክል ተግባራዊ ከሆነ ሀገሪቱን በየአምስት ዓመቱ አፍርሶ የመሥራት የሚመስል ውጤት እንዳያስከትል ጥንቃቄ መወሰድ እንዳለበት ስለታመነበት ሲሆን መራጩ ሕዝብም ከዚህ መግለጫ ተገቢ ግንዛቤ አግኝቶ የሀገሩን መፃዒ ዕድል በተመለከተ የተሻለ ርዕይና አመለካከት ላለው ሰማያዊ ፓርቲ ድምፁን እንዲሰጥ ለማስቻል ነው፡፡
መግለጫው በአራት መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት ተዘጋጅቷል፡፡ የመጀመሪያው የሀገሪቱን ፀጥታ ደህንነት እና ዳር ድንበር በተመለከተ፤ ሁለተኛው የሀገሪቱን ሕግጋት የፍትሕ ሥርዓት የዜጎች ዴሞክራሲና ነፃነትን በተመለከተ፤ ሦስተኛው የሀገሪቱን የመንግስት አስተዳደርና አመራር በተመለከተ እንዲሁም አራተኛው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ሚና እና የአባላቶቻቸውን ተሳትፎ በተመለከተ ሲሆኑ ዝርዘሩ በተራ ቁጥር 6 ስር ተብራርቷል፡፡
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Ethiopia's Blue Party Tries To Reacquaint Nation With Dissent

NPR
Gregory Warner
International Correspondent, East Africa

The Blue Party is one of Ethiopia's few remaining opposition parties. Ethiopia is technically a multiparty parliamentary democracy, like Britain, but it is effectively run like a one-party state, with 99.8 percent of parliamentary seats controlled by one ruling party,......

ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና ከሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ

እንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጸረ ዲሞክራሲ አካሄዱ እየባሰበት የመጣና መሠረታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ማፈኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲ ላይ አገዛዙ በሚያዝዛቸው የተቋማት ኃላፊዎች ቀጭን ትዕዛዝ የፓርቲዎቹ ሕልውና ለጥቂት ግለሰቦች ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ይህ ዓይነቱ ህገ-ወጥ ድርጊት መቼዉም ቢሆን ተቀባይነት አይኖረውም! ለአገራችን የሠላማዊ የስልጣን ሽግግር ከባድ መሠናክል ሊሆን እንደሚችል ሁሉም ይገነዘባል ብለን እናምናለን፡፡ የኢህአዴግ የምርጫ ቦርድ እንዲህ ዓይነቱን ክፉ ስራ ሲወስን የአገራችንን የረጅም ሠላም አይተው ሣይሆን በአገዛዙ ቁንጮ ሰዎች በመታዘዝ በተቋም ስም የሚሠሩት የማደናገር የድንቁርና ተግባራቸዉ አንድ አካል ነው ብለን እናምናለን፡፡ ማህበራችን ይህን ድርጊት እጅጉን ያወግዛል። በመሆኑም ድርጊቱን በጋራ እንቃወማለን።

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በዕጩነት እንዳይቀርቡ ተደረገ

Eng.Yilkal Getnet

• ‹‹ምርጫ በህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በሎተሪ ሆኗል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

Pages

Subscribe to semayawiparty RSS