ምርጫ ቦርድ ከ200 በላይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ሰረዘ

• ‹‹ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ በምርጫ ሂደቱ እንዲቆይ አይፈልግም›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

ሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ እንደተሰረዙበት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በመላ አገሪቱ በተለይም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንች ማጅ፣ በምዕ/ጎጃም፣ በሲዳማ፣ በከምባታ፣ በጋሞጎፋ፣ አዲስ አበባ፣ በደቡብ ጎንደርና ጉጅን ጨምሮ በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ አንድን ዕጩ ለመሰረዝ የሚያበቃ ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት ሳይኖር ‹‹ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ታዘናል›› በማለት ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤትና ለክልል ምክር ቤቶች ያስመዘገብናቸው ዕጩ ተወዳዳሪዎቹን በመሰረዝ ከምርጫው ውድድር ውጪ እንዲሆኑ እየተደረገ እንደሆነ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የትግል ጥሪ አስተላለፈ

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የሁለተኛ ዙር የሠላማዊ ትግል ጥሪውን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተላለፈ፡፡ ትብብሩ የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 ከተሞች ሊያደርገው አቅዶት የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ በሳምንት አራዝሞ ለየካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም ማስተላለፉንም አስታውቋል፡፡

ሰማያዊ ለአንድነት አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ሊያደርግ ነው

ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ቦርድ በአንድነት ፓርቲ ላይ ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ፓርቲን ለተቀላቀሉትን የቀድሞ የአንድነት አባላት እሁድ የካቲት 8/2007 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እንደሚያደርግ ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ፕሮግራሙን ማዘጋጀት ያስፈለገው ምርጫ ቦርድ በአንድነት ላይ በወሰደው እርምጃ ተስፋ ሳይቆርጡ ሰማያዊ ፓርቲን የተቀላቅሉ አባላት ትግሉን ለማጠናከር ያሳዩትን ቆራትነት እና አብሮነት ለማጠናከር እንደሆነ ሊቀመንበሩ ገልጸዋል፡፡

ከጥር 26/2006 ዓ.ም ጀምሮ ፓርቲውን የተቀላቀሉትና አሁንም መቀላቀሉ የሚፈልጉት የቀድሞው የአንድነት አባላት በፕሮግራሙ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረቡት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሁለቱ ፓርቲዎች አባላት በሰማያዊ ፓርቲ ጥላ ስር አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለ ለውጥ እንደሚያመጡ ተስፋቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ምርጫ ቦርድ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን እያገደ ነው

• የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ንግድ ቤት ታሽጓል

ምርጫ ቦርድ በሰማያዊ ፓርቲ ምልክትና ስም የተመዘገቡትን ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንዲታገዱ በየ ክልሉ ለሚገኙ የምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ በላከው ደብዳቤ ገለጸ፡፡ ምርጫ ቦርድ ለደቡብ ክልል የምርጫ ጣቢያ በላከው ደብዳቤ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ትብብር የሚባል መስርቻለሁ፣ እያስተባበርኩ ነው በማለት እንዲሁም ሌሎች የህግ ጥሰቶችን በመፈጸሙ›› በሚል ማስጠንቀቂያ እንደተሰጠው በመግለጽ በፓርቲው ምልክት ሊወዳደሩ የተመዘገቡትን አባላት ህገ ወጥ ናቸው ብሏል፡፡

የምርጫ ሂደቱ በኢህአዴግና በምርጫ ቦርድ ከፍተኛ ችግር እየደረሰበት ነው!

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ሰማያዊ ፓርቲ በ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ የሚያበቃውን ውጤት ለማስመዝገብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ነፃና ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ በመሆን ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ የሚል መርሀ ግብር በማዘጋጀት ምርጫ ቦርድን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ እንዲሆኑ በተለያዩ መንገዶች ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ እስካሁን ከተደረጉት እንቅስቃሴዎችም በተጨማሪ ምርጫ ቦርድና የመንግስት አስፈፃሚ ተቋማት በህገ መንግስቱ በተደነገገው መሰረት ነፃና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩና የፖለቲካ ምህዳሩም ለሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ፍትኃዊ እሰኪሆን ድረስ የነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ ዘመቻችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በሁሉም የሀገሪቷ ክፍሎች እጩ ተወዳዳሪዎችን ለማስመዝገብ ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች በተለያዩ የምርጫ አካባቢዎች በዕጩ ተወዳዳሪዎቻችን ላይ በገዢው ፓርቲ አባላትና በምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ከፍተኛ እንግልትና እንቅፋት የተፈጠሩባቸው ሲሆን ለአብነት ከብዙ በጥቂቱ ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ በፖሊስ እየታደኑ ነው

በዘንድሮው ምርጫ ሰማያዊን ወክለው በመቀሌ ለውድድር የቀረቡት አቶ አስገደ ገ/ስላሴ በፖሊስ እየታደኑ መሆኑን ገለጹ፡፡

አቶ አስገደ አሁን ላይ ከቤታቸው ውጭ ከተማ መውጣታቸውን ገልጸው፣ ቤታቸው ሦስት ፖሊሶች ሄደው ‹‹አቶ አስገደ የት ናቸው? ይፈለጋሉ!›› በሚል አሁንም ድረስ ቤታቸው አካባቢ እየፈለጓቸው መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ጸ/ቤቱን እንዲለቅ ክስ ቀረበበት

• በወር 40 ሺህ ብር ኪራይና 250,000 ብር ለ‹‹ኪሳራ›› እንዲከፍል ተጠይቋል

ሰማያዊ ፓርቲ የካ ክ/ከተማ በቀድሞው መጠሪያው ቀበሌ 15 እንዲሁም በአዲሱ መጠሪያው ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 460 የሆነውን ጽ/ቤቱን 25000 ሺህ ብር ቅጣት ከፍሎ እንዲለቅ በአከራዮቹ በኩል ክስ ቀረበበት፡፡ በከሳሽ እነ አቶ ሚስጥረ ሽበሽ የተመሰረተው ክስ ‹‹ቤቱን ለቀው ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ...በወር ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ሒሳብ ከጥር 16 ቀን 2007 ጀምሮ ቤቱን ለቀው እስከሚያስረክቡ ድረስ ባልተነጣጠለ ኃላፊነት እንዲከፍሉን›› ያሉ ሲሆን ‹‹ከሳሽ ቤቱን ለማደስ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በገባነው ውል መሰረት የደረሰብንን 250 ሺህ ብር ኪሳራ እንዲተኩልን›› ሲሉ ከሰዋል፡፡

የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡
በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት ወዳለው ሰማያዊ ፓርቲ ተቀላቅለው ሰላማዊ ትግላቸውን ለመቀጠል መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
መግለጫውን የ‹ቀድሞው አንድነት ፓርቲ› አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔው አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እንዲሁም የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሌሎችን በመወከል ሰጥተዋል፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች ለአራተኛ ጊዜ 28 ቀናት ቀጠሮ ተሰጠባቸው

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ የሚገኙት የሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀጠና/ዞን አመራሮች ለአራተኛ ጊዜ 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው፡፡
ዛሬ ጥር 19 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት የሰማያዊ (የፓርቲው የጎንደር አደራጅ አቶ አግባው ሰጠኝ)፣ የአንድነት እና መኢአድ የዞን አመራሮች ፖሊስ ‹‹ምስክሮችን ማደራጀት ይቀረኛል›› በሚል ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቆ ለአራተኛ ጊዜ ፍርድ ቤቱ 28 ቀናት ሰጥቷል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በጎንደርና ጎጃም አካባቢዎች የዛሬ ሦስት ወር በፖሊስ ታስረው ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ እንዲዛወሩ የተደረጉ ሲሆን፣ በማዕከላዊ ምርመራ ማዕከል ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የተጠርጣሪ ወዳጆች ተጠርጣሪዎቹን እንዳይጠይቁ አሁንም ድረስ እንደተከለከሉ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ምስራቅ ጎጃም ውስጥ የምርጫ ጣቢያዎች እየተዘጉ መሆኑ ተገለጸ

•‹‹ኢህአዴጎች ለፈለጉት ሰው ቤት-ለቤት እያደሉ ነው››

በምስራቅ ጎጃም ዞን የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተቋቋሙ የምርጫ ጣቢያዎች የመራጭነት ካርድ የሚያወጡ ዜጎችን ‹‹ካርድ ሰጥተን ጨርሰናል›› በሚል ምክንያት ከሁለት ቃናት በፊት ጀምሮ ብዙ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡
ምስራቅ ጎጃም ጎዛምን ወረዳ የቦቅላ የምርጫ ክልል በአብዛኞቹ የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋታቸውን የገለጹት የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች፣ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ ከፍተኛ ወከባ እየደረሰ ነው ሲሉም አክለው ገልጸዋል፡፡

Pages

Subscribe to semayawiparty RSS