Semayawi(Blue) Party’s second successful demonstration

One of this year plans was to awake the public at large into participating in politics without a fear. Of all the methods we engaged in demonstration was one of it. On April 27, 2014, we decided to have the protest.

Free Semayawi(Blue) Party leaders NOW!

Arrested members and leaders of Semayawi(Blue) Party
Free them NOW!

ሰማያዊ ፓርቲ የዞን ዘጠኝ አክቲቪስቶችንና ሌሎች ጋዜጠኞች ላይ እየተደረገ ያለውን እስር አጥብቆ ያወግዛል!

በነገው ስልፍም ይፈቱ ዘንድ ድምጹን ያሰማል!

ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የተነጠቁ መብቶቻችን እናስመልሳለን›› በሚል ሚያዝያ 19 ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ከምናነሳቸው ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሰልፉ ገዥው ፓርቲን ላይ የሠላ ትችት ስለሰነዘሩና ለህዝባቸው መረጃ ስለሰጡ ብቻ የሚደርስባቸውን ህገ ወጥ እርምጃ ያወግዛል፡፡

በሳምንቱ ውስጥ የህዝብን መብት ለማስመለስ ለጠራነው ሰልፍ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ 50 ያህል አመራሮችና አባላት በህገ ወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት የፓርቲያችን ሊቀመንበር (ማታ ተፈትተዋል)፣ ምክትል ሊቀመንበር፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በህገ ወጥ መንገድ መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ በተመሳሳይ ወቅት የዞን ዘጠኝ አክቲቪስቶችና ሌሎች ጋዜጠኞችም ታስረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ሌሎችን ለማሰር ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለሚዲያ ማህበረሰቡ የተላለፈ ጥሪ

ቀን 18/08/ 2006 ዓ.ም

ውድ የሚዲያ ማህበረሰብ አባላት፡- ባለፉት 23 ዓመታት ህወሓት/ኢህአዴግ በህገ መንግስቱ የሚዲያ ነጻነት እንደሚፈቀድ ቢደነግግም በተግባር ግን የራሱን ፕሮፖጋንዳ ከሚነዛባቸው ሚዲያዎች ውጭ ሌሎቹን ሲዘጋና ሲያሸማቅቅ ኖሯል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ህዝባችን ከገዥው ፓርቲ ፕሮፖጋንዳ ውጭ አማራጭ መረጃ ማግኘት አልቻለም፡፡ ጋዜጠኞች እየታሰሩ፣ እየተሰደዱ፣ ሚዲያዎች እየተዘጉም ቢሆን የተቻላችሁን ያህል ለህዝብ መረጃ ለማድረስ የሚዲያው ማህበረሰብ አባላት ለምታደርጉት ሁሉ ከፍ ያለ ክብር አለን፡፡ የታፈነውን የህዝብ ድምጽ ለማሰማት የምታደርጉትን ጥረትም እናበረታታለን፡፡ ሆኖም አሁንም ቢሆን በገዥው ፓርቲ አፋኝነት ምክንያት ህዝባችን የሚገባውን መረጃ እያገኘ አይደለም፡፡ እናንተም በሰበብ አስባቡ ጫና እየደረሰባችሁ እንደሆነ ፓርቲያችን ይገነዘባል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ከአዲስ አበባ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሩ ጋር ተነጋገሩ

ፖሊስ የሰልፉን ኃላፊነት እንደማይወስድ አስታወቀ የአዲስ አበባ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነሩ በትናንትናው ዕለት ‹‹እንነጋገር!›› ያላቸውን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በዛሬው ቀን ቢሮው በሄዱበት ወቅት ‹‹ሙሉ በሙሉ የሰፉን ኃላፊነት ትውስዳላችሁ!›› እንዳላቸው የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ገልጸዋል፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ በኩል የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ብርሃኑና ምክትል ሰብሳቢው አቶ ስለሽ ፈይሳ የቀረቡ ሲሆን ‹‹እኛ ለፖሊስ ያሳወቅነው በሰልፉ ወቅት ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን እንዲቆጣጠር ነው፡፡ እኛ ሀላፊነት ልንወስድ የምንችለው ይዛናቸው ለምንወጣው ጽሁፍና ለምናስተላልፈው መልዕክት ብቻ ነው፡፡ በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት ሰልፉን ሊያደናቅፉ የሚመጡ አካላት ቢኖሩ ይህን ኃላፊነት ሊወስድ የሚገባው ፖሊስ ነው›› የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል፡፡ አስተባባሪዎቹ ፖሊስ ይህን ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ሰልፉን ለማደናቀፍ ሴራ እየተሸረበ ስለመሆኑ አመላካች ነው ሲልም የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ እሁድ ሚያዚያ 19

ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ!
የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልሳለን!!!
እሁድ ሚያዚያ 19 ቀን ከጠዋቱ 3 - 8 ሰኣት
ቦታ ከፓርቲው ጽ/ቤት ተነስቶ በአዋሬ፣ አድዋ ድልድይ፣ ባልደራስ አድርጎ መድረሻው ወረዳ 8 ሜዳ የካ ሚካኤል ታቦት ማደርያ ይሆናል፡፡
ኑ ራሳችንን ነፃ በማውጣት የሀገራችንን እጣ ፈንታ እንወስን!
ሰማያዊ ፓርቲ

ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንም እያሰረ ነው

ፖሊስ ቅስቀሳው ላይ ያልነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችንም እያሰረ ነው፡፡ በትላንትናው እለት በቅስቀሳ ላይ እያሉ የታሰሩትን አባላትና ደጋፊዎች ሁኔታ ለማጣራት ወደ የካ ፖሊስ ጣቢያ ያቀኑ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ፖሊስ አስሯቸዋል፡፡
በዛሬው ቀን ካሳንቺስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት 1. ብሌን መስፍን 2. አስናቀ በቀለ 3. መስፍን 4. ተስፋዬ አሻግሬ 5. እዮብ ማሞ 6. ኩራባቸው 7. ተዋቸው ዳምጤ የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች 1. ፍቅረ ማሪያም አስማማው 2. እያስፔድ ተስፋዬ 3. ጋሻው መርሻ 4. ተስፋዬ መርኔ 5. ሀብታሜ ደመቀ 6. ዘሪሁን ተስፋዬ 7. ጌታነህ ባልቻ 8. ንግስት ወንዲፍራው 9. ሜሪን አለማየሁ ናቸው
(የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ሰልፉ እውቅና እንደተሰጠው የገለጸበት ቅጽ ተያይዟል)

ከሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተላለፈ ጥሪ!

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ለመሆኗ አለም ይመሰክርላታል፡፡ አንቱ የተባሉ ምሁራንን በማፍራት ለዓለም አበርክታለች፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በአለም ካሉ ታላላቅ ዩንቨርስቲዎች እና የምርምር ተቋማት እስከ አመራነት ድረስ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መገኘታቸው ነው፡፡ እነዚህ ምሁራን በተሰማሩበት ስራ መስክ የሚያስመዘግቡት ውጤት እና በስራቸው ተሸላሚ መሆን ላነሳነው ሀሳብ ማጠናከሪያነት ያገለግለናል፡፡ እጅግ የሚያሳዝነውና ልብ የሚሰብረው ግን ሀገራችን ከእነዚህ ውድ ልጆቿ ተገቢውን ዋጋ አለማግኘቷ ነው፡፡ ሀገራችን የወላድ መካን እየሆነች ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሆነ ተብሎ የሚቀነባበር ሴራ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለንግዱ ማህበረሰብ የተላለፈ ጥሪ!

በንግዱ ዓለም ለተሰማራችሁት ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤
በአሁኑ ወቅት ስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ ሁሉንም የኢኮኖሚ መስክ ጠቅልሎ በመያዙ በአገሪቱ ኢኮኖሚ የሚገባችሁን አስተዋጽኦ እያደረጋችሁ እንዳልሆነ እንረዳለን፡፡ ለይስሙላ ብቻ ነጻ ገበያን ‹‹ፈቅጃለሁ!›› የሚለው ገዥው ፓርቲ ኢኮኖሚውን በራሱ ድርጅቶች ተቆጣጥሮ ለስልጣን መቆያ መሳሪያ አድርጎታል፡፡ የመንግስት ድርጅት የሚባሉትም ቢሆኑ ኢኮኖሚው ጠቅልለው ለተመሳሳይ አላማ መሳሪያ በመሆን ላይ ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎም አገራችን ነጻ ገበያና የግል ባለሃብቶች የተዳከሙባት ግንባር ቀደም አገር ሆናለች፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር 9 ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ይዛ ቀርባለች፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር 9 ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ይዛ ቀርባለች፡፡

በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ በፒዲ ኤፍ ለቀናታል
PDF ያንብቧት!

ፕ/ር አለማየሁ፣ ፕ/ር መሳይ፣ አቶ ታዲዮስ ታንቱ፣ ግርማ ሞገስ፣ ታምራት ታረቀኝና ሌሎችም ጥልቅ ትንታኔ ሰጥተውባታል፡፡ ጋዜጣዋ በርዕሰ አንቀጽዋ በፋሲካው ስለ ነጻነት፣ ፍትህ፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን አስበን እንድንውል ትመክራለች፡፡
በጎንደር የሚፈርሱት 30 ሺህ ቤቶች፣ ኢትዮጵያውያን ዛሬም ‹‹አገራችሁ አይደለም ውጡ!›› እየተባሉ መሆናቸውን፣ አርሶ አደሮች መሬታቸውን ያለ ካሳ መነጠቃቸውንና ሌሎች ትኩስ ወሬዎችን አካትታለች፡፡ ሰለሞን ተሰማ ጂ ለዚህ ትውልድ ‹‹ጥራኝ ጎዳናው፣ ጥራኝ መንገዱ›› እንደሚያስፈልገው ይተነትናል፡፡
በላይ ማናዬ በአገልግሎት እጥረትና በሎሎችም ችግሮች ውስጥ ያለውን ህዝብ ‹‹አይ አንተ ህዝብ ትግስትህ!›› በሚል የችግሩን ጥልቀትና የህዝቡን በዝምታ መገዛት ያስነብበናል፡፡ ጌታቸው ሺፈራው ‹‹የዘመኑ የፖለቲካ ሰማዕታቶች››ን ስለ ፖለቲካው ፋሲካ ቅርበትና ርቀት በአንደበታቸው የሚናገሩትን ጽፏል፡፡

የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ደረጀ መላኩ ስለ ኢትዮጵያ ስትራቴጃዊ ጠቀሜታና ከአሜሪካ ጋር ስላላት ግንኙነት ጥልቅ ትንታኔ ሰጥቶባታል፡፡ ሳሙኤል አበበ ‹‹ማጅራት መችው ፖሊስም የህዝብ ነውን?›› በሚል ‹‹ፖሊስ የህዝብ ነው!›› የሚሉትን ይሞግታል፡፡ ሌሎች ጉዳዮችም ተዳስሰውባታል!

Pages

Subscribe to semayawiparty RSS