ከሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለመምህራን የተላለፈ ጥሪ

ለተከበራችሁ የኢትዮጵያ መምህራን በሙሉ!!! ለአንድ አገር ብልጽግና ትምህርት ቁልፍ ስለመሆኑ ለማንም አጠያያቂ አይደለም፡፡ ለዚህም ሲባል መንግስታት ለትምህርት የሚሰጡት ትኩረት በቀዳሚነት ቦታ ላይ ይገኛል፡፡ በአገራችን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ግን ከዚህ ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው፡፡ የትምህርት ፖሊሲ ከመቸውም ጊዜ በባሰ ሁኔታ ለእናንተ ለመምህራኖች የማያሰራ፣ ብቁ የተማረ ዜጋ የማይፈራበትና ለአገርም የማይጠቅም ሆኗል፡፡ ሁሉንም ነገር ለስልጣናቸው በሚያመች መልኩ የሚዘውሩት የወቅቱ ገዥዎች ትምህርት ከንጉሱና በደርግም ጊዜ ከነበረው በባሰ ደረጃ እንዲገኝ አድርገውታል፡፡

ሰማያዊ በፌደራል መንግስቱና በቡለን ወረዳ የመሰረተው ክስ ሀሙስ ፍርድ ቤት ይቀርባል!

ሰማያዊ ፓርቲ በቤንሻንጉል ጉምዝ በህገ ወጥ መንገድ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ወደ ቦታቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱና ተገቢው ካሳ እንዲከፈላቸው በተደጋጋሚ ባካሄዳቸው ሰላማዊ ሰልፎችና ባወጣቸው መግለጫዎች የጠየቀ ሲሆን መንግስት ለጥያቄው ምላሽ ባለመስጠቱ ዜጎቹ የተፈናቀሉበትን ቡለን ወረዳና የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እንዲሁም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ላይ ክስ መስርቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ክሱን ታዋቂው የዓለም አቀፍ የህግ ባለሙያ ዶክተር ያእቆብ ኃይለ ማሪያም ይዘውት የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ቢሮክራሲያዊ ምክንያቶች መዝገብ ሳይከፈትለት እንደቆየ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል፡፡ ...

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር 8

ነገረ ኢትዮጵያ ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮችን ይዛ ቀርባለች፡፡

በተለያየ ምክንያትጋዜጣዋን ኮፒ በዕለቱ ያላገኛችሁ ይኸው መረጃ ይደርሳችሁ ዘንድ PDF ያንብቧት!

- ፕሮፈሰር አለማየሁ፣ ታምራት ታረቀኝ፣ ግርማ ሞገስና ታዲዮስ ታንቱ ጥልቅ ትንታኔዎችን ሰጥተውባታል፡፡
- የተማሪዎች የሰላማዊ ሰልፍ ማቆም አድማ፣ የአርሶ አደሮች ሰቆቃና ሌሎችም አዲስ ወሬዎች ተካተውባታል፡፡
- በላይ ማናዬ የብሄርፌደራሊዝሙን ቅዝምዝሞሽ ይተነትንልናል፡፡
- ዮናታን ተስፋየ ለምን ፈራን ይለናል፡፡
- እያስፔድ ተስፋዬ የስርዓቱን ሰለባዎች (ከማሞ መዘምር እስከበቀለ ገርባ ዳስሷል፼፡፡ -
- ጌታቸው ሺፈራው ኢህአዴግ ምንም እንደማያሟላ ይሞግታል፡፡
- ብርሃኑ ተክለ ያሬድ የእስር ቤት ትዝታውን አቅርቦባታል፡፡ ወጣቱ አቃቤ ህግ የፍትህ ስርዓቱ ፍትህ ያስፈልገዋል ብሏል፡፡
- የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ስራ አስኪሃጅ በደሎች ተዘርዝረውበታል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ

አዲስ አበባ፡- ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹የተነጠቁ መብቶችን እናስመልስ!›› በሚል መሪ ቃል ሚያዚያ 19/2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ከአሁን ቀደም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ምላሽ እንዲሰጣቸው ቢጠይቅም ጥያቄዎቹ ምላሽ ያልተሰጣቸው ከመሆኑም ባሻገር ጭራሹን እየተባባሱ በመምጣታቸውና ህዝብም እየተማረረ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉን መጥራት እንዳስፈለገ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር 7ን በ PDF ያንብቡ!

Negere Ethiopia No - 7

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ደም ለገሱ!

የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እሁድ መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም የበጎ ፈቃድ ደም ልገሳ አደረጉ፡፡ በሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ አስተባባሪነት የተዘጋጀው ይህ ፕሮግራም እሁድ መጋቢት 28 ቀን 2006 ከቀኑ 7 ሰዓት እስከ 9፡ 45 ‹‹በጎ ፍቃደኝነት ለነጻነት›› በሚል መርህ በፓርቲው ጽህፈት ቤት ተከናውኗል፡፡

ዋና ዓላማውን በወሊድ ጊዜ በሚፈጠር የደም መፍሰስ ምክንያት የሚከሰት የእናቶች ሞትን ለመቀነስ መሆኑን የፓርቲው የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ ሀና ዋለልኝ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የለጋሾቹ ምስል በከፊል

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር 5ን በ PDF ያንብቡ!

ነገረ ኢትዮጵያ ቁጥር - 5 ቁልፍ አገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮችን ይዛ እነሆ በ PDF ያንብቧት

- መዝሙረ ኢህአዴግ!
(በላይ ማናዬ)
- የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ከአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት በተደረገላቸው ግብዣ ወደ አሜሪካ ያመራሉ፡፡ በጉዞው ዓላማና በተለያዩ የአገራችን ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
- ኢትዮጵያና የዩክሬኑ ግጥምጥሞሽ
ባለ ቀለሙን አብዮት ማን ይመራዋል?

(በጌታቸው ሺፈራው)
- አዲስ ጠብመንጃ በምንሽር፤
አገዳደሉ ሆድ የሚያሽር፡፡

(በዝክረ ታሪክ አምድ፡- አቶ ታዲዎስ ታንቱ)
- “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ዘመቻ”
(ግርማ ሞገስ)
- ኑሮ ሆነብን እሮሮ
(ጋሻው መርሻ)
- የኢትዮጵያ ፖለቲካና የሴቶች ተሳትፎ
(ኤልሳቤት ወሰኔ)
- ሰላማዊ ትግሉ መሪዎቹን ይሻል
(ታምራት ታረቀኝ)
- ኢትዮጵያዊነት ለእኔ!
(አፈወርቅ በደዊ)
- እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ፕሮግራሞች የሚተዋወቁበት ገጽ አለልዎት
መልካም ንባብ !

Membership Registration

1. Download and fill out this form
2. Pay membership using donate button from the right side of this page. You can setup auto payment in monthly bases.
Minimum membership fee፡ $30.00 per month
3. Email the form to info@semayawiparty.org

Eng Yilkal is barred from boarding his flight to the US

Semayawi Party Chaiman, Eng Yilkal Getnet was barred from boarding his flight to the United States on Friday, March 21, 2014 at Addis Ababa airport. He was scheduled to fly to the US to attend a fellowship program of the Young African Leaders Initiative of the United States State Department. Eng. Yilkal was told to see a TPLF supervisor by airport crew right before boarding time where he was told he would not be flying. His luggage was unloaded from the plane and he stayed at the airport for more than 3 hours thereafter questioned by TPLF agents. He has returned back to his home after 2:00am local time Saturday.

ለነፃነት የምናደርገው ትግል በህገ ወጥ እስርና ማስፈራሪያ አይደናቀፍም!


በሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ዛሬ መጋቢት 12/2006 ዓ.ም እረፋዱ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ::

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

‹‹ማርች-8›› የሴቶችን ነጻነትና እኩልነት እንዲሁም ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ የሚከበር የሴቶች ቀን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህን በዓል አስመልክቶ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፈው ዕሁድ የካቲት 30/2006 ዓ.ም ሴቶች ብቻ የሚሳተፉበት የጎዳና ላይ ሩጫ ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ የሐገራችንም ሆነ የዓለም ሴቶች የነጻነት ቀናቸውን በሚያከብሩበት ዕለት እንደሌሎች ሴቶች ሁሉ የሰማያዊ ፓርቲ አአባላትም አላማውን ደግፈው በዕለቱ ቀኑን አስመልክቶ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ በዚህ በሴቶች የነጻነት ቀን በስርዓቱ ላይ የሚነሱ ብሶቶችን ካሰሙት ተሳታፊዎች ውስጥ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሚገኙበት ሲሆን፣ በተለየ መልኩ በእነዚህ አባላቶቻችን ላይ ያነጣጠረ የአፈሳ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንደዚህ አይነት ህዝባዊ መድረኮችን ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሌም ህዝብ ላይ የሚደርሰው በደል በማጋለጥ መብት እና ለአገራችን ብሄራዊ ጥቅም በመቆም በገዥው ፓርቲ ተደጋጋሚ ህገ ወጥ እርምጃ ሲወሰድበት ቆይቷል፡፡ የተደረገው ህገ ወጥ ድርጊት ከዚሁ ፓርቲው ለህዝብና ለአገር መቆሙን ተከትሎ እየደረሰበት ያለው የከፋ የጭቆና አካል ነው፡፡

Pages

Subscribe to semayawiparty RSS