ሐውልቱ ሥር ሆኜ እነዚያን ሰማዕታት ሳስብ!

ስድስት ኪሎ አደባባይ የካቲት-12 ሰማዕታት ሐውልት ሥር ሆኜ ያን ዘመንና የወቅቱን አሰቃቂ ድርጊት ባሰብኩ ጊዜ ስቅጠት ተሰማኝ፡፡ የቆመው ሐውልት ማንን ለመዘከር እንደተጀነነ ባወኩ ጊዜ ደግሞ አንገቴን ቀና አድርጌ እኔም እንደ ሐውልቱ መጀነን ከጀለኝ፡፡ እናማ ሐውልቱ ሥር ሆኜ....ስሜቴ ዝብርቅርቅ ነው፤ ቋንቋዬ ብዙ ነው፤ መንፈሴ ጠንካራ ሐዘኔ መራራ ነው፤ ምናቤ የኋሊት ጎታች ምኞቴ ወደ ፊት ሸምጣጭ ነው፤ ሐውልቱ ለኔ የውስጠቱን ይገልጥልኛል፤ ታሪኩን ይነግረኛል....የተጋድሎ ታሪክ ይተርክልኛል፡፡
እንዲህ እያለ....

በጎንደር ከተማ የጠራውን ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ

የሰማያዊ ፓርቲ መንግስት ከህዝብ ጀርባ የሚያካሂደውን የኢትዮጵያ - ሱዳን ድንበር ማካለልን በመቃወም በጎንደር ከተማ የጠራውን ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል በእለቱም የፓርቲው አስተባባሪ ለህብረተሰቡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅትና አምባገንን ስርዓት ውስጥ ሆናችሁ የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል ብላችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን በሚል ንግግር ፕሮግራሙን ከፍተው የሰልፉን አላማ አብራርተው የፓርቲውን ሊቀመንበር ወደ መድረክ ጋብዘዋል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበርም ለተሰላፊዎቹ ባስተላላፉት መልእክት ለወጣቶች የሀገራቸውን ክብር እንዲያስጠብቁ እራሳቸውንም ከፍርሀት እና ከስጋት በማላቀቅ ለራሳቸውም ለሀገራቸውም አለኝታ እንዲሆኑ፤ እንዲሁም ስርዓቱ ላይ ያሉት አስተዳደሮች ስልጣን ወቅታዊ መሆኑን አውቀው በኢትዮጵያ ድንበር ላይ እየተፈጸመ ያለውን ደባ እንዲያስቆሙ ከታሪክ ተጠያቂነት እንዲድኑ፤ ለልጆቻቸውም ውርደትን ሳይሆን ክብርን እንዲያወርሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ፓርቲውም የጠራውን ሰልፍ እና ማስተላለፍ የፈለገውን መልእክት በተሳካ ሁኔታ አስተላልፎ ፕሮግራሙን አጠ

የጥር 25 ቀን የጎንደር ሠላማዊ ሠልፍ ቅስቀሳ እንደቀጠለ ነው!

የጥር 25 ቀን የጎንደር ሠላማዊ ሠልፍ ቅስቀሳ እንደቀጠለ ነው!
በጎንደር ከተማ በነገው ዕለት የሚካሄደውን የሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሠልፍ ቅስቀሳ ለማካሄድ እየተንቀሳቀሰ ያለው ቡድን ሥራውን ለማሰናከል በመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ክትትል እና ወከባ እየተደረገበት ነው፡፡
እንደሚታወቀው የፓርቲው አመራሮች እና አባላት እራሳቸውን በተለያየ ቡድን በማደራጀት የመጡበትን ተልዕኮ ለማሳካት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በዚህም መሠረት በቅስቀሳው ላይ ያለው ቡድን በከተማው ልዩ ልዩ ስፍራዎች ስራውን እያከናወነ ሲገኝ ነገር ግን የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ቅስቀሳውን ለማደናቀፍ የተለያዩ ሙከራ በማድረግ ላይ ቢሆኑም እስካሁኑ ሰዓት ድረስ ቡድኑ በከፍተኛ ቆራጥነት አፈናውን ተቋቁሞ በመስራት ላይ ይገኛል ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በጎንደር ከተማ

በጎንደር ከተማ ለሰአታት በወረዳ 2 ፖሊስ ጣቢያ በቁጥጥር ስር የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እና አባላት አመሻሹ 12 ሰዓት ላይ የተለቀቁ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅትም ሁሉም ባረፉባቸው ሆቴሎች እንደሚገኙ ከአካባባው የተላከው መረጃ አረጋግጣል፡፡ ሆኖም የከተማው ከንቲባ ቢሮ ከዚህ በኋላ ምንም አይነት ቅስቀሳ ማድረግ እንደማይችሉና በሚመጣው እሁድም ምንም አይነት ሰልፍ ማድረግ እንደማይችሉ በቅድመ ሁኔታ እንደለቀቃቸው የገለጸ ሲሆን፤ አመራሮቹ ግን በሀገሪቷ ህግ መሰረት ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ ማንኛውንም ቅስቀሳ ማድረግ ስለማይቻል ከነገ ጠዋት ጀምሮ ግን በዛሬው እለት ተቋርጦ የነበረውን ቅስቀሳ እንሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡ ፖሊስም እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ ምንም እንኳ ታጋቾቹን የለቀቀ ቢሆንም የድርጅቱ ንብረት የሆኑትን ላፕቶፖች እና ካሜራዎች እንዳልመለሰ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Blue Party leaders and members are arrested in the town of Gonder

Blue Party leaders and members of the campaign for peaceful public demonstration at Gonder Mesqel square are arrested in the town of Gonder. They are all now at the "woreda 2" police station in Gonder, four executive leaders of the party are among them. Police also took the cameras and laptops of blue party. The party leaders and members went to Gonder yesterday to hold the public demonstration on February 2, 2014 with the people of the town on issue of Ethio-Sudan border demarcation.

ሰማያዊ ፓርቲ በጎንደር ከተማ ሰልፍ ጠራ

ሰማያዊ ፓርቲ በጎንደር ከተማ ሰልፍ ጠራ፡፡ ሕወሓት ኢህአዴግ በህገ ወጥ መንገድ ሉዓላዊ መሬታችንን ለሱዳን መንግስት አሳልፎ አሳልፎ ለመስጠት እያደረገ ያለውን ህገወጥና ሀገር ቆርሶ የመስጠት ወንጀል በመቃወም ሰማያዊ ፓርቲ እሁድ ጥር 25 2006 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ ማዘጋጀቱን የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ብርሀኑ ተክለ ያሬድ ገለፁ፡፡የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አያይዘው እንደገለፁት ቅዳሜ ጥር 17 2006 ዓ.ም በፓርቲው ፅህፈት ቤት የፓናል ውይይት እንደሚደረግና በነዚህ ፐሮግራሞች ላይም የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲቪክ ተቋማትና ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲሳተፍ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ሻ/ል አየለ ማሞ አረፉ!

ሻ/ል አየለ ማሞ አረፉ! ትላንት ጥር 10 ቀን 2006 ዓ.ም. በ74 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሻ/ል አየለ ማሞ በተለያዩ የፖሊስና የወታደራዊ ማዕረጎች ሀገራቸውን ያገለገሉ ሲሆን፣ የሰማያዊ ፓርቲ መስራችና የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ነበሩ፡፡ የቀብር ስነሥርዓታቸው ዛሬ ጥር 11 ከረፋዱ በ4፡00 በጀሞ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለትግል ጓዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ

የሰማያዊ ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል የህዝብ ግንኙነት በሆኑት በአቶ እምላዕሉ ፍስሐ ጋር ተወያዩ

ማክሰኞ ጥር 14 ቀን 2006 ዓ.ም. ከረፋዱ አራት ሰአት ጀምሮ እስከ አምስት ሳአት ተኩል ድረስ በድሬደዋ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ውስጥ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል የህዝብ ግንኙነት በሆኑት በአቶ እምላዕሉ ፍስሐ እና በሰማያዊ ፓርቲ የድሬደዋ ቅርንጫፍ ጊዜአዊ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል የፓርቲውን የእስካሁን ድረስ እንቅስቃሴና ያጋጠሙ ችግሮችን ተወያይተዋል፡፡ በቀጣይነትም ከጥንካሬአችን እና ከድክመታችን ተምረን ምን መሰራት እንዳለበት የተለያዩ ሀሳቦች ቀርበው ጊዜአዊው ጽህፈት ቤቱ የከተማውን ህብረተሰብ ማዕከል ባደረገ መልኩ በንቀሳቀስ እንደሚጠበቅበት ተስማምተዋል፡፡

በኢትዮ- ሱዳን ድንበር ዙሪያ ወቅታዊና ትምህርታዊ የውይይት መድረክ

ሰማያዊ ፓርቲ በኢትዮ ሱዳን ጉዳይ ላለፉት ወራት ነገሩን በቅርበት ሲከታተል የቆየ ሲሆን በጉዳዩም ላይ አቋሙን በመግለጫ መልክ ማውጣቱ ይታወሳል አክሎም ፊታችን ጥር 25 ቀን ለቦታው ቅርበት ካላቸው ከተሞች አንዷ በሆነችው ጎንደር ከተማም ተቃውሞ ሰልፍ መጥራቱ ይታወቃል፡፡ ከነዚህ አንቅስቃሴዎች በተጨማሪም ድንበራችንን ጉዳይ በተመለከተ በተጨባጭ መረጃ በህብረተሰቡ ውስጥ ግንዛቤ ይፈጠር ዘንድ ትምህርታዊ ውይይት መድረክ ያዘጋጀ ሲሆን በዝግጅቱ ላይም በዘርፉ ለረጅም አመታት በመስራት የሚታወቁት የረጅም ጊዜ የጆግራፊ ባለሞያ የሆኑት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ድንበሩን በተመለከተ ሰፋ ያለ ትምህርት ይሰጣሉ፡፡ እርስዎም በዝግጅቱ ላይ እንዲሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ቀን፡- ቅዳሜ ጥር 17 ቀን
ሰዓት፡- ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡- በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት

On Behalf of Semayawi Party, Thanks! (By Prof.Al Mariam)

Thank you one and all who came out to the town hall meetings in the U.S. and Europe over the past several weeks and supported Semayawi Party!
In a report last week, Ethiomedia.com described Semayawi Party (SP) as the “newest opposition sensation” which “raises new hopes” for nonviolent change in Ethiopia. Yilikal Getnet, Semayawi Party’s young and dynamic chairman, presented Ethiopians in various U.S. and European cities his party’s vision of the Beloved New Ethiopia founded on hope, peace and unity.

Pages

Subscribe to semayawiparty RSS